አባል ሀገራት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ሁሉም ዐይነት ጥቃቶችን የሚከለክሉ ሕጎችን ለማውጣት እና ለማስፈጸም ተገቢ እና ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው
States Parties shall take appropriate and effective measures to enact and enforce laws to prohibit all forms of violence against women
Women have the right to a peaceful existence and the right to participate in the promotion and maintenance of peace
ሴቶች በሰላም የመኖር እንዲሁም ሰላምን በማስፋፋትና በማስጠበቅ ሥራዎች ላይ የመሳተፍ መብት አላቸው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በወንጀል ፍትህ ሥርዓት ውስጥ የጥቃት ተጎጂ ሴቶች እና ህፃናትን መብቶች አያያዝን በተመለከተ ያደረገውን የክትትል ሪፖርት ይፋ አደረገ
በወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ በወንጀል ሥነ ሥርዓትና በማስረጃ ደንቦች ባለመካተታቸው፣ የጥቃት ተጎጂ ሴቶችና ሕፃናት ፍትሕ እንዳያገኙ ማድረጉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (አሰመኮ) አስታወቀ
የጥቃት ተጎጂ ሴቶች እና ሕፃናት በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ውስጥ ሲያልፉ መብቶቻቸውን በተሟላ መልኩ የሚያስጠብቁ ሕጎች እና አሠራሮች ያስፈልጋሉ
በሃዲያ ዞን ግርዛትን ለማስቀረት ተጀምረው የነበሩ የመከላከልና የንቅናቄ ሥራዎች መቀነስ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ግርዛት ስርጭት እንዲጨምር አስተዋጾ አድርጓል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገልጿል
አብዛኛዎቹ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር የሚከወኑ ስራዎች ከድንበር ማሻገር ያሉት ላይ ያተኮረ እንደሆነ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናግሯል
በወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ ውስጥ የጥቃት ተጎጂ ሴቶችና ሕፃናት ሰብአዊ መብቶች አያያዝን ለማሻሻል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር ያስፈልጋል