ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት ሰፊ የምርመራ ሪፖርት ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ በቅርቡ በአፋርና በአማራ ክልሎች የተካሄዱ ጦርነቶችን የተመለከተ አዲስ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡
የሰብአዊ መብቶችን በማስከበር ረገድ ሚና ያላቸው የሰብአዊ መብቶች ተቋማት እንዲሁም በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትም በሴት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ላይ መረጃ የመሰብሰብ፣ የክትትል ሥራዎች እና ጥሰቶችን የማጋለጥ ሥራዎች መስራት አለባቸው።
ፍትሕ እና የተጎዱ ሰዎችና ቦታዎችን መልሶ መጠገን የሁሉንም ወገኖች ቁርጠኝነት ይፈልጋል
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት የታሰሩ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል
ኮሚሽኑ ዓላማውን ለማስፈጸም ከሚሰራቸው ሰብአዊ መብቶችን የማስተማር እና የማስፋፋት ስራ ውጤታማ እንዲሆን ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በአጋርነት የሚሰራ ሲሆን፣ ከሀገራዊ የኪነጥበብና የሥነ ጥበብ ባለሞያዎችና ማኅበራት ጋር የሚያደርገውን ትብብር በተመሳሳይ መልኩ እኩል ክብደት የሚሰጠው ነው
በአዋጁ ምክንያት የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ ከጠየቁት መካከል የአሜሪካ መንግሥት እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ይገኙበታል።
ከእስር ከተለቀቁት መካከል ሴቶች፣ አረጋውያን፣ የጤና ችግር ያለባቸው እና ሌሎች ጉዳያቸው ተጣርቶ በቀላል ዋስትና የተለቀቁ ሰዎች ይገኙበታል
ለባለፉት በርካታ ወራት ሰፊ አካታች ሂደት ሲዘጋጅ የቆየው ይህ የስትራቴጂ እቅድ ኮሚሽኑ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሊሰሩና ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብሎ የለያቸው ቁልፍ የውጤት መስኮችንና ዋና ዋና ተግባራትን አካቷል።
በአጠቃላይ ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል ለማረጋገጥ እንደቻለው ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መተግበር ባለበት መንገድ በተለይም “የጥብቅ አስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነት እና ከመድልዎ ነፃ መሆን” የሚሉትን የሰብአዊ መብት መርሆዎችን ባከበረ መልኩ አለመተግበሩን ተመልክቷል።
ኢሰመኮ በማቋቋሚያ አዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ወቅት ሰብአዊ መብቶችን የሚከታተል መሆኑንና የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ለኮሚሽኑ የክትትል ተግባራት ትብብር የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ለማስታወስ ይወዳል