ስልጠናዎቹ ሰብአዊ መብቶችን እና የሰብአዊ መብቶች እሴቶችን መሠረት በማድረግ የሰልጣኞችን ዕውቀት፣ ክህሎት እና አመለካከት ለመገንባት ያለሙ ናቸው
በክልል ውድድሮች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ስምንት ትምህርት ቤቶች ከግንቦት 12 እስከ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚካሄደው ሀገራዊ ውድድር ተሳታፊ ይሆናሉ
በተለያዩ አካባቢዎች እየተባባሱ ናቸው ለተባሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈጻሚውን አካል እንዲጠይቅና እንዲያሳስብ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥያቄ አቀረበ
በአማራ ክልል፣ “የሕግ ማስከበር” በሚል በፌዴራሉ መንግሥት እየተወሰደ ያለው ወታደራዊ ርምጃ፣ በጣም አሳሳቢ እንደኾነና ችግሩ በውይይት እንዲፈታ፣ ኢሰመኮ የተወካዮች ምክር ቤትን አሳሰበ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዐበይት ክንዋኔዎችና ውጤቶች | 2014 ዓ.ም.  
በመፈናቀል ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ሕፃናት የትምህርት አገልግሎት እንዲያገኙ እና ወደ መደበኛ የትምህርት ሥርዓት እንዲመለሱ የሁሉንም ጥረት ይፈልጋል
አባል ሀገራት የሴት ልጆች በትምህርት ቤቶችና በሌሎች ማሰልጠኛ ተቋማት ቅበላና ማቆያን ማበረታታ እንዲሁም ትምህርታቸውን ያለጊዜው ላቋረጡ ሴቶች ሌሎች መርኃ-ግብሮችን ማዘጋጀት አለባቸው
ስምምነቱ የሰብአዊ መብቶች እሴቶችን ወደ ማኅበረሰቡ ከማስረጽ አኳያ ተደራሽነትን በመጨመር በኢትዮጵያ ዘላቂና ውጤታማ በሆነ መንገድ የሰብአዊ መብቶች ባህልን ለማስፈን ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው
ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ለአደጋ የተጋለጡ እና ብዙውን ጊዜ ለመብቶቻቸው መከበር የተለየ ድጋፍ እና ጥበቃ ካልተደረገ ለተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የመዳረጋቸው ዕድል የሰፋ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የክልል ሰንደቅ ዓላማን የመስቀል እና ክልላዊ መዝሙርን የማስዘመር እርምጃ የሕግ መሠረት የሌለው ነው ሲል ኢሰመኮ ገለጸ