ሁሉም ወገኖች ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ለሰላም አማራጮች ቅድሚያ እንዲሰጡ፣ ግጭቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ፣ የክልሉን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ በመንግሥት የሚወሰዱ እርምጃዎች በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን ነዋሪዎችን ለበለጠ ጉዳት እና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዳይዳርጉ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ ያሳስባል
በተለያዩ አካባቢዎች ያለው የሰላም መደፍረስ፤ ካለኝ የተመጠነ በጀት እና የሰው ሀይል በላይ በስራ እንድወጠር አድርጎኛል ሲል ኢሰመኮ ተናገረ
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅትም ሰብአዊ መብቶች ሊከበሩና ለግጭቶች ዘላቂ መፍትሔ ለሰላማዊ ውይይት ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል
የሕግ አስከባሪ ተቋማት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁንና ደንቡን በሥራ ላይ ሲያውሉ እና ሲያስፈጽሙ ከዚህ በታች በተመለከቱት የሰብአዊ መብቶች እና ሕገ መንግሥታዊ መርሖች እንዲመሩ፣ በማናቸውም ሁኔታ ሊገደቡ የማይችሉ መሠረታዊ መብቶችን እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ፣ እንዲሁም በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜትና የሙያ ሥነ ምግባር እንዲመሩ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በከፍተኛ አደራ ጭምር እያሳሰበ አፈጻጸሙንም በስልታዊ መንገድ የሚከታተል መሆኑን ይገልጻል፡፡  
በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች የተቀበሩና የወዳደቁ ፈንጂዎች በአፋር ክልል 27 ሰዎችን፣ በአማራ ክልል ቁጥራቸው ያልተገለፀ ሰዎችን ለሞት እንዲሁም ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
በሰው የመነገድ ወንጀል ማለት ግለሰቦችን ለብዝበዛ በማስገደድ፣ በመጥለፍ፣ በማታለል ወይም በኃይል በመመልመል፣ በማጓጓዝ፣ በማሸጋገር፣ በመቀበል፣ ወይም በማስጠለል የሚፈጸም ድርጊት ነው
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች የተቀበሩ ፈንጂዎችን የማጽዳቱ ሥራ በአስቸኳይ መጠናቀቅ እንደሚኖርበት አሳስቧል
በሰው የመነገድ ወንጀል ሰለባ የሆኑ ሰዎች ሰብዓዊ መብታቸው ተከብሮ የተሟላ ድጋፍ እና ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ
ወንጀሉን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የተዘጋጀው ረቂቅ የስትራቴጂ ዕቅድ ጸድቆ ወደ ሥራ ሲገባ የጥበቃና ድጋፍ ሥርዓት እንደሚዘረጋ ይጠበቃል
ከበጀት ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ቅንጅታዊ አሠራር እና አማራጭ የቅጣት ውሳኔዎችን በሰፊው ሥራ ላይ ማዋል ጉልህ ሚና አለው