ለሟቾች ቤተሰቦች እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ለደረሰባቸው ጉዳት ተገቢ የሆነ ካሳ ሊሰጣቸው ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ በኅዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም. የከረዩ የሚችሌ ገዳ አባላት አርዳ ጅላ ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሕይወትና የአካል ጉዳት ስለመፈጸሙ በደረሰው ጥቆማ መሰረት፣ ከታኅሣሥ 7 እስከ ታኅሣሥ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. በቦታው በመገኘት ምርመራ አካሂዷል።
ጥር 14 ፣ 2014 ዓ.ም.፣ ጅግጅጋ፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር የሕግ ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አድንቋል።
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥሪ አቀረበ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመንግስት የቀረበለትን ውሳኔ ሃሳብ በአፋጣኝ እንደሚያጸድቀው ኮሚሽኑ ተስፋውን እየገለጸ፤ የመንግስት ስራ አስፈጻሚ አካላት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ አሁንም በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ጥሪውን ያቀርባል
ከእስር ከተለቀቁት መካከል ሴቶች፣ አረጋውያን፣ የጤና ችግር ያለባቸው እና ሌሎች ጉዳያቸው ተጣርቶ በቀላል ዋስትና የተለቀቁ ሰዎች ይገኙበታል
Persons released include women, older persons, persons with health problems and others released on citation following an investigation.
Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) Public Statement | December 16, 2021
ኮሚሽኑ አያይዞም የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ የሰብአዊ መብቶችን መርሆች ባከበረ መልኩ መተግበሩን የሚመለከታቸው አካላት በቅርብ ሊከታተሉ እና ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ያስተላለፈውን ጥሪ በድጋሚ አስታውሷል።