https://www.facebook.com/ethiopianewsagency/posts/pfbid0xW7Lke8VCrCgSYwAhNr2g76bhZ1kAAac1YWHU5ZkWfGnrH5ub1oWHAfTsTYcvFxel

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከፍትሕ ሚኒስቴር እና ከፍሬድሪክ ኤልበርት ስቲፍታንግ (Friedrich Elbert Stiftung) ጋር በመተባበር የንግድ እና የሰብአዊ መብቶች ብሔራዊ የድርጊት መርኃ ግብር ዝግጅት ማስጀመሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል። የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፤ ለሰብአዊ መብቶች ትኩረት የሰጠ የንግድና የልማት አሠራርን ማስቀጠል ተገቢ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም የመንግሥት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የሃይማኖት መሪዎችና ሌሎችም ቅንጅታዊ ጥረት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል