የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 41(3) 

የኢትዮጵያ ዜጐች ሁሉ በመንግሥት ገንዘብ በሚካሄዱ ማኅበራዊ አገልግሎቶች በእኩልነት የመጠቀም መብት አላቸው፡፡

የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳንአንቀጽ 25 

ማንኛውም ዜጋ በዘር፣ በቀለም፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም ሌላ አመለካከት፤ በብሔራዊም ሆነ ማኅበራዊ አመጣጡ፣ በሀብት፣ በትውልድ ወይም በሌላ መለኪያ ምንም ልዩነቶች ሳይደረጉበትና አግባብነት የሌላቸው ገደቦች ሳይደረጉበት በሀገር ውስጥ ለሕዝብ በተዘረጉ አገልግሎቶች በእኩልነት የመጠቀም መብትና ዕድል ይኖረዋል፡፡

Equal Access to Public Services