የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 38(1 (ሀ))
- ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቀለም፣ በዘር፣ በብሔር፣ በብሔረሰብ፣ በፆታ፣ በቋንቋ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሌላ አመለካከት ወይም በሌላ አቋም ላይ የተመሠረተ ልዩነት ሳይደረግበት በቀጥታ እና በነጻነት በመረጣቸው ተወካዮች አማካኝነት በሕዝብ ጉዳይ አስተዳደር የመሳተፍ መብት አለው።
ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ አንቀጽ 21(3)
- የመንግሥት አስተዳደር ሥልጣን መሠረቱ የሕዝብ ፍቃድ መሆን ይኖርበታል፤ የሕዝቡ ፍቃድ የሚገለጸውም በተወሰኑ ጊዜያት በሚካሄዱ ሐቀኛ ምርጫዎች ነው።