
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣው መግለጫ ሰሞኑን ባደረገው ክትትል በአማራ ክልል፣ በአዊ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር፣ በተፈጠረው ብሔር ተኮር ግጭት ሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን እንዲሁም በኢንቨስትመንት ቦታዎች ላይ ጉዳት መድረሱን፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ኢመደበኛ የአማራ ታጣቂዎች መሆናቸው የተገለጸ ያላቸው ቡድኖች በሰነዘሩት ብሔር ተኮር ጥቃት እና ይህንኑ ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት በርካታ በሚል በቁጥር ያልገለፃቸው ሰዎች ላይ የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት መድረሱን ገልጿል