ኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ እና የባህላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 11 (1) እና (2) 

  • ማንኛውም ሰው በቂ ምግብ፣ ልብስና መኖሪያ ቤትን ጨምሮ ለራሱና ለቤተሰቡ በቂ የኑሮ ደረጃ የማግኘት መብት አለው።
  • የዚህ ቃል ኪዲን ተዋዋይ ሀገራት ማንኛውም ሰው ሳይራብ ለመኖር ያለውን መሠረታዊ መብት በመገንዘብ በተናጠልም ሆነ በዓለም አቀፍ ትብብር አማካኝነት፦
    • ቴክኒካዊና ሳይንሳዊ ዕውቀትን በሙሉ በመጠቀም የምግብ አመራረት፣ ክምችትና ስርጭት ዘዴን ለማሻሻል፣ የአልሚ ምግብ መሠረታዊ ዕውቀቶችን ለማሰራጨት፣ ከፍ ያለ ውጤት ያለው የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና አጠቃቀም እንዲኖር የግብርና ሥርዓቱን ለማሻሻል፤  
    • ምግብ አስመጪና ላኪ ሀገራት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ግምት ውስጥ በማስገባት በፍላጎታቸው መሠረት ፍትሐዊ የዓለም የምግብ አቅርቦት ስርጭት እንዲኖር ለማረጋገጥ ዝርዝር መርኃ ግብሮችን ጨምሮ አስፈላጊ እርምጃዎችን ይወስዳሉ።