በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አዘጋጅነት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምስለ-ችሎት (Moot Court) ውድድር በሕግና ሰብአዊ መብቶች ባለሞያዎች የሚዳኝ ከሞላ ጎደል የመደበኛ ፍርድ ቤት ክርክር ሥርዓትን የሚከተል አስተማሪ የውድድር አይነት ነው። ተወዳዳሪ ተማሪዎች ተገቢው ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ ምናባዊ በሆኑ የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ (hypothetical case) ላይ ተመስርተው አመልካች እና ተጠሪን በመወከል የጽሑፍ እና የቃል ክርክር የሚያደርጉበት ነው።
ይህ ቪዲዮ በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ዙርያ ያተኮረውን እና ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ የተካሄደውን የሁለተኛ ዙር የፍጻሜ ዝግጅት ያሳያል።