Skip to content
Facebook Twitter
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • SNNP
        • Tigray
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social and Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants Rights
        • Rights of Persons with Disabilities and the Rights of Older Persons
        • Women’s and Children’s Rights
        • HR Monitoring and Investigation
        • Human Rights Education
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • Events
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል:- በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ለውሃ አቅርቦት ጥያቄ ሰልፍ የወጡ ነዋሪዎች ላይ በጸጥታ ኃይሎች በተወሰደ ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ ለደረሰው የሕይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል

February 17, 2023February 17, 2023 Press Release

ተመሳሳይ ዓይነት የመብት ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ ለጸጥታ ኃይሎች ግልጽ አመራር ማስተላለፍ ያስፈልጋል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች የቧንቧ ውሃ አቅርቦት ከወር በላይ ለሆነ ጊዜ መቋረጡን ተከትሎ ላጋጠማቸው የውሃ ችግር መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ለማቅረብ ሰልፍ በወጡ ነዋሪዎች ላይ በፖሊስ በተወሰደ የኃይል እርምጃ በነዋሪዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ ኢሰመኮ የዐይን ምስክሮችን፣ ተጎጂዎችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን እና የጤና ባለሙያዎችን በማነጋገር ባሰባሰበው መረጃ እና ማስረጃ መሠረት 3 ሰዎች ጭንቅላታቸውና ደረታቸው ላይ በጥይት ተመተው የተገደሉ ሲሆን ቢያንስ በ30 ሰዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው የአካል ጉዳት መድረሱን አረጋግጧል፡፡

የአካባቢው ባለሥልጣናት በበኩላቸው ለደረሰው ጉዳት ምክንያት የሆነው ከሰልፈኞች ውስጥ የተወሰኑት ሰዎች የከተማው የውሃ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ላይ ድንጋይ መወርወራቸውን እና የመኪና መንገድ መዝጋታቸውን ተከትሎ በክልሉ ፖሊስ በተወሰደ የኃይል እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የተወሰደው የኃይል እርምጃ ከነገሩ ሁኔታ አንጻር ሲታይ ተመጣጣኝ ያልሆነ መሆኑን ገልጸው “አንገብጋቢ በሆነ የውሃ አቅርቦት ጥያቄ ሰልፍ ወጥተው ድንጋይ በወረወሩና መንገድ በዘጉ ሰዎች ላይ ሕይወት የሚያጠፋ መሣሪያ ተጠቅሞና ጥይት ተተኩሶ ነዋሪዎች መገደላቸው ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እርምጃ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት አስቸኳይ ማጣራት አድርጎ በአጥፊዎች ላይ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ እና የተጎዱ ሰዎችም ተገቢውን ካሳ ሊያገኙ ይገባል” ብለዋል፡፡ ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም ለወደፊቱም ተመሳሳይ ዓይነት የመብት ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ ለጸጥታ ኃይሎች ግልጽ አመራር እንዲተላለፍ ያስፈልጋል በማለት አሳስበዋል፡፡

Location SNNP

Related posts

June 17, 2022October 6, 2022 EHRC Quote
ጋምቤላ ክልል፡ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈጸሙ የኃይል እርምጃዎች
September 6, 2022October 6, 2022 Press Release
ኦሮሚያ ክልል፡ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ኡሙሩ ወረዳ በታጠቁ ቡድኖች በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመ ጥቃት
August 26, 2021February 12, 2023 Press Release
ምስራቅ ወለጋ፡ የነዋሪዎችን ደኅንነት ለማረጋገጥ የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ሊጠናከር ይገባል
August 11, 2020February 11, 2023 Press Release
"በወላይታ ዞን የጸጥታ ሃይሎች በተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል ከመጠቀም ሊቆጠቡ ይገባል!"-ኢሰመኮ

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on Twitter

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
EHRC
We are an independent national human rights
institution tasked with the promotion & protection of
human rights in Ethiopia
Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org

© 2023 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in settings.

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Gambella
    • Oromia
    • Somali
    • SNNP
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social and Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants Rights
    • Rights of Persons with Disabilities and the Rights of Older Persons
    • Women’s and Children’s Rights
    • HR Monitoring and Investigation
    • Human Rights Education
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Videos
    • Newsletters
    • Events
  • Resources
Facebook Twitter
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.