የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተሻሻለው የማቋቋሚያ አዋጁ አንቀጽ 6 መሠረት በምርጫ ወቅት የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ዙሪያ ክትትል የማድረግ ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በዚህም መሠረት በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅን የሚከታተል የባለሙያዎች ቡድን ወደ ቦታው አሰማርቷል።

ከሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ጋር ተያይዞ ዜጎች ሕጋዊ ያልሆኑ ጣልቃ ገብነቶች፣ እቀባዎች እና ክልከላዎች ቢያጋጥሙ ለኮሚሽኑ ባለሙያዎች ማሳወቅ የሚችሉ ሲሆን ነጻ የስልክ መስመር 7307 ላይ በመደወልም መረጃ እና ጥቆማዎችን ማድረስ ይቻላሉ።