ማንኛውም ሰው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ በመከልከሉ ወይም ከኢትዮጵያ ለቆ እንዲወጣ ወይም ወደመጣበት እንዲመለስ በመደረጉ ወይም በማናቸውም ሌላ እርምጃ ምክንያት፡-

ሀ) ዘሩን፣ ሃይማኖቱን፣ ዜግነቱን፣ የአንድ ማኅበራዊ ቡድን አባልነቱን ወይምም የፖለቲካ እምነቱን ምክንያት በማድረግ ማሳደድ፣ መሰቃየት ወይም መንገላታት ወደ ሚደርስበት ሀገር፣ ወይም

ለ) በውጭ ወረራ፣ በግዛት መያዝ፣ በወጭ አገዛዝ ወይም የሀገሪቱን ሕዝባዊ ሥርዓት ወይም ፀጥታ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በከባድ ሁኔታ በሚያናጋ ሁኔታ ሕይወቱ፣ አካሉ፣ ስብዕናው ወይም ነፃነቱ አደጋ ላይ ወደሚወድቅበት ሀገር እንዲመለስ ወይም በዚያው እንዲቆይ የሚያስገድደው ከሆነ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ አይከለከልም ወይም ከኢትዮጵያ ለቆ እንዲወጣ ወይም ወደመጣበት እንዲመለስ አይደረግም።

(የስደተኞች ጉዳይ አዋጅ= 1110/2011 አንቀጽ 11 (ሀ) እና (ለ))

Non-refoulement/Non-Forceful Repatriation of Refugees


Photo credit: Frank Keillor