ዓለም አቀፍና ሀገራዊ የሲቪክ ማኅበረሰባትና የሰብአዊ መብቶች ተቋማት በሙያ አጋርነት፣ በዘርፉ ያሉትን እድገቶችና አሠራሮች በማስተዋወቅና በማሻሻል እንዲሁም የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች ግንዛቤና እውቀትን በማስፋፋት ረገድ ለኮሚሽኑ ቁልፍ አጋር ናቸው።
ይህ ቪዲዮ ኮሚሽኑ ዓላማውን ለማስፈጸም ይረዳው ዘንድ ከተለያዩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት፣ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶችን ጨምሮ ዓለም አቀፍና እና አህጉራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ጋር በመተባበር የሚያከናዉናቸውን ተግባራት በአጭሩ ያሳያል።
International and national civil society and human rights institutions in professional partnership play a key role by integrating new developments and procedures in the sector and in the promotion of human rights issues.
This video shows EHRC’s partnership with key stakeholders for an impactful human rights work.