የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 36(1)  

ሁሉም ሕፃናት:-

  1. በሕይወት የመኖር፣
  2. ወላጆቻችውን ወይም በሕግ የማሳደግ መብት ያላቸውን ሰዎች የማወቅና የእርነሱንም እንክብካቤ የማግኘት፣
  3. ጉልበታቸውን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፣ በትምህርት፣ በጤናቸውና በደኅንነታቸው ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎች እንዲሠሩ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ፣ እና 
  4. በትምህርት ቤቶች ወይም በሕፃናት ማሳደጊያ ተቋሞች ውስጥ በአካላቸው ከሚፈጸም ወይም ከጭካኔና ኢ-ሰብአዊ ከሆነ ቅጣት ነጻ የመሆን መብቶች አሏቸው።