የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 12(2)

አባል ሀገራት ከታች የተዘረዘሩትን የተወሰኑ አዎንታዊ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው፦ 

  • በሴቶች መካከል ማንበብና መጻፍን/ ማስፋፋት፣ 
  • በሁሉም ደረጃዎችና በሁሉም የትምህርት ዘርፎች በተለይም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ትምህርትና ስልጠናዎችን ለሴቶች ማስፋፋት፣ 
  • የሴት ልጆች በትምህርት ቤቶችና በሌሎች ማሰልጠኛ ተቋማት ቅበላና ማቆያን ማበረታታ እንዲሁም ትምህርታቸውን ያለጊዜው ላቋረጡ ሴቶች ሌሎች መርኃ-ግብሮችን ማዘጋጀት አለባቸው። 

በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ስምምነት፣ አንቀጽ 10

  • አባል ሀገራት ሴቶች በትምህርት መስክ ከወንዶች እኩል ያላቸውን መብቶች ለማረጋገጥ በሴቶች ላይ የሚደረጉ አድሎዊ ልዩነቶችን ለማስወገድ ተገቢ የሆኑ እርምጃዎችን ሁሉ መውስድ አለባቸው።