ማንኛውም ሕፃን በግጭት ወቅትም በሕይወት የመኖር ተፈጥሯዊ የሆነ መብት አለው፡፡ ሀገራት የሕፃኑን ሕልውና እና እድገት በተቻላቸው መጠን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ 

በተ.መ.ድ. የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት፤ በግጭት ወቅት በሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ስድስት ከባድ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡፡ 

  • ሕፃናትን መግደል እና አካል ጉዳተኛ ማድረግ፣ 
  • ሕፃናትን ለውትድርና መቅጠር ወይም ማዋል፣ 
  • በሕፃናት ላይ ወሲባዊ ጥቃት ማድረስ፣ 
  • ሕፃናትን መጥለፍ፣ 
  • በትምህርት ቤቶች እና የጤና ተቋማት ላይ ጥቃት ማድረስ፣ 
  • የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለሕፃናት መከልከል