የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 27(3) 

ወላጆች እና ለሕፃኑ ኃላፊነት ያለባቸው ሌሎች አካላት የሕፃኑን ለእድገቱ ተስማሚ የሆነ በቂ የኑሮ ደረጃ የማግኘት መብት እንዲያሟሉ ለማገዝ፣ አባል ሀገራት እንደየሀገራዊ ሁኔታቸው እና ዐቅማቸው ተገቢውን እርምጃ ይወስዳሉ። አስፈላጊ በሆነ ጊዜም በምገባ፣ በአልባሳት እና በመጠለያ ረገድ ቁሳዊ ድጋፍ ያደርጋሉ፤ የድጋፍ መርኃ ግብሮችንም ያዘጋጃሉ።  

የአፍሪካ የሕፃናት መብቶችና ደኅንነት ቻርተር፣ አንቀጽ 11(3)(መ) 

አባል ሀገራት የሕፃናትን የመማር መብት ሙሉ በሙሉ እውን ለማድረግ ሁሉንም ተገቢ እርምጃዎች ይወስዳሉ። በተለይም በትምህርት ቤት ተገኝቶ ትምህርትን በቋሚነት መከታተልን ለማበረታታት እንዲሁም የተማሪዎችን ትምህርት የማቋረጥ ምጣኔ ለመቀነስ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው።