የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 36 

ማንኛውም ሕፃን ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፤ በትምህርቱ፣ በጤናውና በደኅንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎች እንዲሠራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ መብት አለው።

አስከፊ የሆኑ የሕፃናት ጉልበት ሥራን በተመለከተ በዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት የወጣ ስምምነት ቁጥር 182/1999፣ አንቀጽ 3 

አስከፊ ከሆኑ የሕፃናት ጉልበት ሥራዎች መካከል ማንኛውም ዐይነት የባርነት ወይም ባርነትን የመሰሉ ተግባራት፣ የሕፃናት ንግድ እና ሕገ ወጥ ዝውውር፣ ሕፃናትን በእዳ እና በግዴታ አገልጋይነት መያዝ፣ እንዲሁም ሕፃናትን በኀይል በማስገደድ ወይም ግዴታን ለማሟላት የጉልበት ሥራ ማሠራት እና ለጦርነት ዓላማ መመልመል የሚሉት ይገኙበታል።