የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 22 (1) (2) 

  • ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በማኅበር የመደራጀት ነጻነት አለው፡፡ ይህም ጥቅሞቹን ለማስጠበቅ የሠራተኛ ማኅበራትን የማቋቋም እና አባል የመሆን መብትን ይጨምራል፡፡
  • በሕግ ከተደነገገው እና በዴሞክራሲያዊ ማኅብረሰብ ውስጥ ለብሔራዊ ደኅንነት፣ ለሕዝብ ሰላምና ጸጥታ ጥቅም ወይም የሕዝብን ጤናና ሥነ ምግባር ወይም የሌሎችን መብቶችና ነጻነቶች ለመጠበቅ አስፈላጊ ከሆነው በቀር በዚህ መብት አጠቃቀም ላይ ምንም ዐይነት ገደብ አይደረግበትም፡፡