ስለ እኛ


የሰብአዊ መብቶች ትምህርት

የሰብአዊ መብቶች ትምህርት ፕሮግራም ሰብአዊ መብቶችን የማክበር ባሕልን ማጠናከርና በባለመብቶችና በባለግዴታዎች ዘንድ ስለ ሰብአዊ መብቶች እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ማሳደግን ዓላማ ያደረገ ነው።

ውጤታማ፣ ስልታዊና ሀገር-አቀፍ የሆነ የሰብአዊ መብቶች ትምህርት ፕሮግራም ስልጠናዎች፣ ሴሚናሮች፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄዎችና የሰብአዊ መብቶች ትምህርት በብሔራዊ የትምህርት ፖሊሲና ሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ እንዲካተት የውትወታ ስራዎች መስራትንም ያካትታል። አሳታፊና ተግባር-ተኮር የትምህርትና ስልጠና ዘዴዎችን ጨምሮ አዳዲስና መሰረታዊ ለውጥ አምጭ የስልጠና አሰጣጥ ሥነ-ዘዴዎች እንዲሁም ግብዓቶችን በመጠቀም በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን የማክበር ባሕል እንዲዳብር አስፈላጊ የሆነውን የአመለካከትና የባህሪ ለውጥ ማረጋገጥ ይቻላል።