ስለ እኛ


የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ

ዓለም አቀፍ እና ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች እየተከበሩ መሆናቸውንና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአግባቡ መመርመራቸውን ለማረጋገጥ ከግለሰቦች በሚቀርቡልን አቤቱታዎች ላይ በመመስረት ወይም በኮሚሽኑ አነሳሽነት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምርመራ እናደርጋለን፣ በእስር ቤቶች እና ለሕዝብ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት ክትትል እናደርጋለን። በክትትል እና የምርመራ ሥራዎቻችን የመብት ጥሰት የደረሰባቸው ሰዎች መፍትሔ እንዲያገኙ፥ ሰብአዊ መብት የጣሱ ሰዎች ደግሞ ተጠያቂ እንዲሆኑ እናደርጋለን።

ማንኛውም ግለሰብ ወይም ተቋም ኮሚሽኑ በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ለሚያከናውናቸው የክትትል እና ምርመራ ስራ የመተባበርና የማገዝ ግዴታ አለበት።