ስለ እኛ


የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች

የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ፕሮግራም የሲቪልና ፖለቲካ መብቶችን የማስፋፋት፣ የማክበርና የማስከበር ዓላማ አለው። በሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ፕሮግራም የሚሰራባቸው ሰብአዊ መብቶች የመደራጀትና የመንቀሳቀስ ነፃነት፣ ሃሳብን የመግለጽ ነፃነት እና መረጃ የማግኘት መብት፣ በሕይወት የመኖር፣ የነፃነትና የደኅንነት መብት፣ የሕግ እኩል ጥበቃ እንዲሁም ፍትሕ የማግኘት መብቶች፣ በፖለቲካ እንዲሁም በመንግስት አሰራሮች የመሳተፍ እና ከአድሎና ኢሰብአዊ ከሆነ አያያዝ የመጠበቅ መብቶችን ያካትታሉ። 

በጥናትና ምርምር፣ በሰብአዊ መብቶች ምርመራ እና ውትወታ፣ ውጤታማ የሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን በመከወን እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር ትብብር በመፍጠር የሲቪልና ፖለቲካ መብቶችን ለማስፋፋት እንሰራለን። በተጨማሪም ለሕግ የበላይነትና ለዲሞክራሲ መዳበር መሰረት የሆነውን ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንሰራለን።