ስለ እኛ


የሴቶች እና ሕጻናት መብቶች

ሴቶችም ሆኑ ሕጻናት በከፍተኛ ሁኔታ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጋላጭ በመሆናቸው፣ የሴቶችንና የሕጻናትን ሰብአዊ መብቶችን ማስፋፋት፣ ማክበርና ጥበቃ ማድረግ ለሰብአዊ መብቶች ስራ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራት ናቸው።

ቁልፍ የሆኑ ስትራቴጂያዊ ተግባራት የሕጎች ጥናት፣ ሥርዓታዊ የመብት ጥሰቶችን መመርመር፤ ሕጎችና አሰራሮች ከዓለም-አቀፍና ከብሔራዊ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ጋር የሚጣጣሙ መሆኑን መከታተል፤ ማብቃትና የሴቶችና ሕጻናት መብቶችን በሁሉም ደረጃ ባሉ አሰራሮች ማካተት እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር ትብብርን መፍጠርና ማጠናከርን ይጨምራል።