ስለ እኛ


የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋዊያን መብቶች

ከአጠቃላይ ሕዝብ ቁጥር 17.6% የሆነው አካል ጉዳተኛ በሆነበት እንዲሁም ለአረጋዊያን የሚደረገው ጥበቃና እንክብካቤ ውስን በሆነበት ሁኔታ፥ የአረጋውያን መብቶችን እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች መብቶችን ማስፋፋት፣ ማክበርና ማስከበር ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።  

ውጤታማ የሆነ የምርምር ስራ፣ ውትወታ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ትብብሮችን የማጠናከር ተግባራትን ተመጋጋቢ በሆነ መንገድ በመከወን፥ እነዚህ አብይ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚገጥሟቸው ፈርጀ ብዙ ተግዳሮቶች በተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠር፤ ችግሮቻቸውም የብሔራዊ ፖሊሲ ቀረፃ አጀንዳ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲሁም አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ሰብአዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ የሕግና ተቋማት መሻሻያዎች እንዲደረጉ እንሰራለን።