የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 9(2) 

  • ማንኛውም ሰው በሚያዝበት ጊዜ የተያዘባቸውን ምክንያቶችና የቀረቡበትን ክሶች ምንነት ወዲያውኑ የማወቅ መብት አለው፡፡ 

የኢ... ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 19(2 እና 3) 

  • የተያዙ ሰዎች ያለመናገር መብት አላቸው፤ የሚሰጡት ማንኛውም ቃል ፍርድ ቤት በማስረጃነት ሊቀርብባቸው እንደሚችል መረዳት በሚችሉት ቋንቋ እንደተያዙ ወዲያውኑ እንዲያውቁት መብት አላቸው። 
  • የተያዙ ሰዎች በ 48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብት አላቸው። ይህም ጊዜ ሰዎቹ ከተያዙበት ቦታ ወደ ፍርድ ቤት ለመምጣት አግባብ ባለው ግምት የሚጠይቀውን ጊዜ አይጨምርም።