የአፍሪካ የሰዎች እና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የአረጋውያን መብቶች ፕሮቶኮል፣ አንቀጽ 7 

አባል ሀገራት፦ 

  • ከሥራ ገበታቸው የሚሰናበቱ አረጋውያን በቂ የጡረታ አበል እና ሌሎች የማኅበራዊ ዋስትና ዓይነቶች እንዲኖሯቸው የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎችን እና ሕጎችን ማውጣት፤ 
  • ለየትኛውም ዓይነት የማኅበራዊ ዋስትና አገልግሎት አስተዋጾ ለማድረግ ዕድል ላላገኙ አረጋያን የገቢ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ የማኅበራዊ ጥበቃ አገልግሎት ሥርዓት መዘርጋቱን ማረጋገጥ፤ 
  • የጡረታ አበል የማግኘት ሂደቶች እና ሥነ ሥርዓቶች ያልተማከለ፣ ቀላል እና አክብሮት የታከለባቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ፤ 
  • ግለሰቦች በአረጋዊነት ጊዜ ገቢ እንዲኖራቸው ለማስቻል የሕግ ማውጣት እና ሌሎች እርምጃዎችን መውሰድ እና 
  • አረጋውያን ከመንግሥት አገልግሎት ሰጪዎች አገልግሎቶችን የማግኘት መብቶቻቸውን የሚያመቻቹ የሕግ እና ሌሎች እርምጃዎች የመውሰድ ግዴታ አለባቸው።