የአካል ጉዳተኞች መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 7 

  • አባል ሀገራት አካል ጉዳተኛ ሕፃናት ከሌሎች አቻዎቻቸው ጋር በእኩል ደረጃ የሁሉም ሰብአዊ መብቶችና መሠረታዊ ነጻነቶች ሙሉ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ሁሉ ይወስዳሉ፡፡ 
  • አካል ጉዳተኛ ሕፃናትን በሚመለከቱ እርምጃዎች ሁሉ የበለጠ ቅድሚያ ተሰጥቶት የሚታየው ጉዳይ የራሳቸው የሕፃናቱ ዘላቂ ጥቅምና ፍላጎት ይሆናል፡፡ 

የአፍሪካ ሕፃናት መብቶችና ደኅንነት ቻርተር፣ አንቀጽ 13 

ማንኛውም አእምሮው ወይም አካሉ የተጎዳ ሕፃን ከመንፈሳዊና ከአካላዊ ፍላጐቱ ጋር የተጣጣመ እንዲሁም ክብሩን የሚያረጋግጥ፣ በራስ መተማመኑንና በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ተሳትፎ የሚያሳድግ የተለየ የጥበቃ እርምጃ ተጠቃሚ የመሆን መብት አለው፡፡