Skip to content
Facebook Twitter
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • SNNP
        • Tigray
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social and Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants Rights
        • Rights of Persons with Disabilities and the Rights of Older Persons
        • Women’s and Children’s Rights
        • HR Monitoring and Investigation
        • Human Rights Education
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • Events
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የአዲስ ዓመት መልእክት

September 12, 2022October 7, 2022 Public Statement

ለመላው የኢሰመኮ ባልደረቦች፣
ኮሚሽኑን በተለያየ መንገድ የሚያግዙ አጋር ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት፣
እንኳን ለ2015 ዓ.ም. አደረሳችሁ!

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

በአሁኑ ወቅት ትምህርት ቤቶች ለአዲሱ ዓመት ተመልሰው በሚከፈቱበት ወቅት ላይ ብንሆንም በርካታ ሕፃናት እና ታዳጊዎች በግጭት፣ በመፈናቀል፣ በድርቅ ምክንያት ወይም በኑሮ ውድነት አልያም በሌሎች ችግሮችና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በመሆናቸው ምክንያት ወደ ትምህርት ቤት አይገቡም ወይም አይመለሱም። በጦርነት እና በግጭቶች ሳቢያ የወደሙባቸው ትምህርት ቤቶቻቸው፣ የጤና ተቋማቶቻቸው እና የተቋረጡባቸው መሰረተ ልማቶችና አገልግሎቶች እንዲጠገኑ በመጠበቅ ላይ ያሉ ልጆቻችን በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው።

ከግማሽ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ18 ዓመት በታች እንደመሆኑ መጠን ይህ የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በማንኛውም የሥራ ዓይነት እና በተለይም በመንግሥት ሥራ ላይ ባለን ሰዎች ላይ ተጨማሪ እና አፋጣኝ የሆኑ ኃላፊነቶችን የሚጥል ነው።

ከእነዚህ መካከል ዋነኛው በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ያሉ ሕፃናት ሰላም አግኝተውና ደኅንነታቸው ተጠብቆ ለመኖር እንዲችሉ ጥረት ማድረግ እና የተጀመሩ ጥረቶችን በማንኛውም መንገድ መደገፍን የሚመለከተው ነው። ለሀገራችን ሰላም የአቅማችንን የምናደርገው ድጋፍ በቀጥታ ተሳትፎ የምናከናውናቸውና ፍትሕና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ወይም ዘላቂ የመልሶ ማቋቋም ተግባራት እንዲከናወኑ ማድረግ ወይም ለተጎዳ አንድ ቤተሰብ የልጆች ደብተር በመግዛት በግላችን የምናደርገው ድጋፍ ሊሆን ይችላል። አልያም በአካባቢያችን፣ በድረ ገጾች ወይም በሕትመት በምናስተላፋቸው መልእክቶች እና ንግግሮች አማካኝነት ሊሆንም ይችላል።

በአሁኑ ወቅት እኛ እራሳችን ሕፃናት እና ልጆች ከነበርንበት ወቅት በእጅጉ በተለየ መልኩ እያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን በቴክኖሎጂ እና በኢንተርኔት ተቀርጾ የሚቀርና  የእኛ ልጆች ለአካለ መጠን ሲደርሱ ፈልገው ማግኘት የሚችሉት መሆኑ ልጆችን እና ታዳጊዎችን በተመለከተ ያለብንን ኃላፊነት ክብደት የሚጨምር ነው። ልጆቻችን አድገው በኢንተርኔት የታሪክ ማኅደር የተናገርነውን እና ያደረግነውን በማየት እንዳይሸማቀቁ፣ ይልቁንም ክብር እና ኩራት እንዲሰማቸው ከማድረግ የበለጠ የሚያስጨንቅ ኃላፊነት ሊኖር አይችልም።

ልጆቻችን ለአካለ መጠን በሚደርሱበት ወቅት ስለሚጠብቃቸው ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ከባቢያዊ ሁኔታ መተንበይ ባይቻልም የሕዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረበት፣ የአየር ለውጥ በሁሉም መልኩ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድርበት፣ በቴክኖሎጂ እድገት አማካኝነት የተለያዩ አዳዲስ ምቾቶችን ማግኘት የሚችሉበት ሆኖም በዚያው ልክ የሥራ ዕድሎች ውስንና አዳዲስ እና ከፍተኛ ደረጃ ክህሎቶችን የሚጠይቁበት እንደሚሆን የታወቀ ነው።

ልጆቻችንን ለዚህ ለመጪው ጊዜ ተወዳዳሪ መሆን እንዳይችሉ ወይም የሌሎች ሀገራት ወጣቶች ከሚጓዙበት የእድገት ፍጥነት እንዲዘገዩ የሚያደርጉ ሁኔታዎችን ለመቅረፍ ገና ብዙ እርምጃዎች፣ ሥራዎች እና ኃላፊነቶች ይጠብቁናል። ትምህርት ቤቶችን የመጠገኑ፣ የመገንባቱ እና ተያያዥ መሰረተ ልማቶችን የማቋቋሙ፣ የትምህርት ጥራትን የማረጋገጡ እንዲሁም ትምህርት ቤቶች ልጆቻችን ለአዕምሮአቸው እድገት ጭምር አስፈላጊ የሆኑትን ንጥረ ነገሮች የያዙ ምግቦችን እና መሰረታዊ የጤና አገልግሎትን የሚያገኙበት ቦታ እንዲሆኑ ማስቻሉ ዕቅድ፣ ሃብት  እና ረዘም ያለ ጊዜ የሚጠይቅ ሊሆን ይችላል።

ሆኖም በእያንዳንዱ የትምህርት ቤት አስተዳደር፣ መምህራን እና ሠራተኞች እንዲሁም በሚመለከተው የመንግሥት አካል ፍቃድ አማካኝነት እና እገዛ ብቻ፣ ቢያንስ ሀገራችን በምትገኝበት ፈታኝ ጊዜ ውስጥም ጭምር እና በሥራ ላይ ባሉ የትምህርት ተቋማት ውስጥ፣ ትምህርት ቤቶች ልጆቻችን መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች መርሆችን፣ አብሮ መኖርን እና መዋደድን የሚያዩበትና የሚኖሩበት እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል። ይህ እንዲሆን የትምህርት ተቋማቶች ከአነሳሽ፣ ግጭት ጠንሳሽ ንግግሮች የጸዱ እንዲሆኑ ማድረግ፣ ይልቁንም ተቋማቱ ልጆቻችን ሊሄዱ የሚጓጉበት እና የተሳትፎ፣ የፈጠራና የመዝናኛ ጊዜ የሚያገኙበት፣ እንዲሁም በሥነ ምግባራቸውና በአሠራራቸው ምሳሌ የሚሆኗቸውን ሰዎች የሚያዩበት ቦታ እንዲሆኑ ማድረግ ተጨማሪ ሃብትም ሆነ የተራዘመ ዕቅድ አይጠይቅም።

ስለሆነም፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባልደረቦቼ ስም በተቋማችን ላይ የተጣለውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የአቅማችንን ሁሉ እንደምናደርግ ስገልጽ ለሁሉም ወገኖች ይህንን የሰላም ጥሪ እና መልካም ምኞት በማስተላለፍ ነው።

Location Ethiopia

Reports & Press Releases

September 6, 2022October 7, 2022 Event Update
የአፍሪካ የሰዎች እና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር እና የአፍሪካ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል አፈጻጸምን አስመልክቶ በአባል ሀገር መንግሥታት ለአፍሪካ የሰዎች እና የሕዝቦች መብቶች ኮሚሽን በሚቀርበው ወቅታዊ ዘገባ አዘገጃጀት ዙሪያ የተዘጋጀ አውደ ጥናት
April 27, 2022October 6, 2022 Human Rights Concept
Business and Human Rights
August 26, 2021February 20, 2022 ጋዜጣዊ መግለጫ
ምስራቅ ወለጋ፡ የነዋሪዎችን ደኅንነት ለማረጋገጥ የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ሊጠናከር ይገባል
September 30, 2020May 12, 2021 ጋዜጣዊ መግለጫ
ኢሰመኮ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ህልፈት ሐዘኑን ይገልጻል

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on Twitter

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
EHRC
We are an independent national human rights
institution tasked with the promotion & protection of
human rights in Ethiopia
Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org

© 2023 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in settings.

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Gambella
    • Oromia
    • Somali
    • SNNP
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social and Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants Rights
    • Rights of Persons with Disabilities and the Rights of Older Persons
    • Women’s and Children’s Rights
    • HR Monitoring and Investigation
    • Human Rights Education
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Videos
    • Newsletters
    • Events
  • Resources
Facebook Twitter
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.