
የጉዟቸው ዓላማም በዋናነት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኮምሽኑ ጋር በመተባበር ከግንቦት 12 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚቆይ “የዳኝነት ነጻነት ለሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ያለው አንደምታ እና ተያያዥ ጉዳዮች …” ላይ ለፍርድ ቤቶች : ለፍትሕ ቢሮ: ለፖሊስና ሌሎች ለሚመለከታቸው ተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እና ለባለድርሻ አካላት በተዘጋጀው ወርክሾፕ ላይ ለመሳተፍ ሲሆን ዋና ኮሚሽነሩ እና ባልደረቦቻቸው ባሕር ዳር ሲገቡ የአማራ ብሔራዊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ አለምአንተ አግደው እና ባልደረቦቻቸው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል