የተያዙ ሰዎች በዋስ የመፈታት መብት አላቸው፡፡ ሆኖም ግን በሕግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች ፍርድ ቤት ዋስትና ላለመቀበል ወይም በገደብ መፍታትን ጨምሮ በቂ የሆነ የዋስትና ማረጋገጫ እንዲቀርብ ለማዘዝ ይችላል፡፡ (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት፤ አንቀጽ 19(6))

በወንጀል ክስ ምክንያት የታሰረ ወይም በቁጥጥር ስር የሚገኝ ማንኛውም ሰው በዳኛ ወይም በሕግ የዳኝነት ሥልጣን በተሰጠው አካል ፊት በአፋጣኝ የመቅረብ፤ እንዲሁም ተገቢ በሆነ ጊዜ ውስጥ ዳኝነት የማግኘት ወይም የመለቀቅ መብት አለው፡፡

የፍርድ ሂደት የሚጠብቁ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማቆየት እንደ መደበኛ አፈጻጸም ሊታይ አይገባም፤ ይሁን እንጂ ከእስር መለቀቁ ግለሰቡን ጉዳዩ በፍርድ ቤት በሚታይበት ጊዜ እንዲቀርብ፤ ወይም ፍርዱ እንዲፈጸምበት ለማድረግ በሚያስችል የዋስትና ማረጋገጫ ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይችላል፡፡ (ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት አንቀጽ 9(3))