ሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ስምምነት፣ አንቀጽ 14

  • ይህን ስምምነት የተቀበሉ ሀገራት የገጠር ሴቶች ያሉባቸውን ልዩ ችግሮችና የቤተሰቦቻቸውን ኢኮኖሚያዊ ሕልውና በማስጠበቅ በኩልና በገንዘብ ያልተተመነ የሀገሪቱ ክፍለ ኢኮኖሚ ውስጥ ጭምር ያላቸውን ከፍተኛ አስተዋጽዖ ግምት ውስጥ በማስገባት የዚህን ስምምነት ድንጋጌዎች ለገጠር ሴቶች ተፈጻሚነታቸውን ለማረጋገጥ ተገቢውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ፡፡
  • ይህን ስምምነት የተቀበሉ ሀገራት በገጠር ሴቶች ላይ የሚደረግ አድሎአዊ ልዩነት በማጥፋት ሴቶች ከወንዶች እኩል በገጠር ልማት እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲሳተፉና ከዚሁም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ተገቢውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ፡፡