የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው በአንድ መቶ ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም፤ እስካሁን ድረስ አለመፈታታቸውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የሚከተለውን ብለዋል ፡፡
‹‹የሰብዓዊ መብቶች መከበር ዋና ዋስትናው የፍርድ ቤት ውሳኔ መከበር በመሆኑ፤ አቶ ልደቱ
አያሌውን ጨምሮ በፍርድ ቤት የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸውና የዋሰትና ሁኔታውን አJልተው
ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሰጠላቸው ታሳሪዎች በሙሉ በአስቸኳይ እና ያለምንም
ቅድመ ሁኔታ ከእስር ሊፈቱ ይገባል››