የፕሬስ መብት ጥበቃን እውን ለማድረግ፣ በሚዲያ አማካኝነት ተፈጽሟል ለተባለ ወንጀል የተጠረጠረን ማንኛውንም ሰው በቅድመ ክስ ወይም በቅድመ ፍርድ እስር ማቆየትን የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ሕግ ይከለክላል፡፡

በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ወይም አካል በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆይ ሳይደረግ ክሱ በቀጥታ በዓቃቤ ሕግ አማካኝነት ለፍርድ ቤት መቅረብ አለበት፡፡ (የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013፣ አንቀጽ 86(1))

ይህ ክልከላ ለፕሬስ፣ ለመገናኛ ብዙኃን እና ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ ሰብአዊ መብት ልዩ ጥበቃ የሚያደርግ ነው፡፡