
በምክክር መድረኩ የተገኙት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ በሁሉም ማዕከላት የሰብዊ መብቶች አያያዝን በማሻሻል ለህግ ታራሚዎች ደንብና መመሪያዎችን ከማስተዋወቅ ጀምሮ የመድሃኒት አቅርቦትን በማሻሻል እንዲሁም የግንባታ ስራዎችን ከማፋጠን አኳያ ለተሰሩ ስራዎች እና በኮሚሽኑ የሚሰጡ ምክረ ሃሳቦች ስራ ላይ በመተግበራቸው ምስጋና አቅርበዋል