Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

በሚያዝያ ወር ከመንግሥት፣ ከሲቪክ ማኅበረሰብ እና ከሚድያ አካላት ጋር በአፋርና ኦሮሚያ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ የተደረጉ ውይይቶች

May 16, 2022October 5, 2022 Event Update

በሰሜን ኢትዮጵያ ከተከሰተው ጦርነት ጋር ተያይዞ በተደረጉ ምርመራዎች የተሰጡ ምክረ ሃሳቦችን ክትትል በተመለከተ፣ ለፕሬስ ነፃነት እና ለሚዲያ ሥራ ያለው ሀገራዊ አውድ እንዲሁም የዘላቂ ልማት ግቦች እና ሰብአዊ መብቶች ተያያዥነት በውይይቶቹ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል ናቸው

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

ቢሾፍቱ
በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደ ውይይት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከተባበሩት መንግሥታ ድርጅት ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት (OHCHR) ጋር በመተባበር በዘላቂ የልማት ግቦች እና በሰብአዊ መብቶች መካከል ያለው ተመጋጋቢነት እና ክትትል ላይ በተመለከተ ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ተወያይቷል።

በዚህም መሰረት እ.ኤ.አ. 2030 ለማሳካት የተቀረጹት ዓለም አቀፍ የዘላቂ ልማት ግቦች አመጣጥ የታወሰ ሲሆን፣ በተለይም የልማት ግቦቹን የሀገር አቀፍ ደረጃ አፈጻጸም ክትትል ለማድረግ የተቀመጡት አመለካከቾች በሰብአዊ መብቶች ላይ ለሚሰሩ ድርጅቶች የሰብአዊ መብቶች ክትትል ለማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ተገልጿል።

ቢሾፍቱ
በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደ ውይይት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከተባበሩት መንግሥታ ድርጅት ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት (OHCHR) ጋር በመተባበር በዘላቂ የልማት ግቦች እና በሰብአዊ መብቶች መካከል ያለው ተመጋጋቢነት እና ክትትል ላይ በተመለከተ ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ተወያይቷል።

በዚህም መሰረት እ.ኤ.አ. 2030 ለማሳካት የተቀረጹት ዓለም አቀፍ የዘላቂ ልማት ግቦች አመጣጥ የታወሰ ሲሆን፣ በተለይም የልማት ግቦቹን የሀገር አቀፍ ደረጃ አፈጻጸም ክትትል ለማድረግ የተቀመጡት አመለካከቾች በሰብአዊ መብቶች ላይ ለሚሰሩ ድርጅቶች የሰብአዊ መብቶች ክትትል ለማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ተገልጿል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት በኢትዮጵያ ሁኔታ የሚዲያ መስፋፋት እንዲሁም የሕግ ማዕቀፍ መሻሻሉ እንደ ጥሩ ጅማሬ የሚጠቀስ የነበረ ቢሆንም አሳሳቢ ሁኔታዎች ግን መምጣታቸውን ጠቁመዋል፡፡ በተለይም የጋዜጠኞች በዘፈቀደ መታሰርና መፈታት መበራከቱ እና ጋዜጠኞችን ማዋከብ እና ማስፈራራት አሳሳቢ እየሆነ እንደመጣ ዋና ኮሚሽነሩ አንስተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ከተነሱት ተግዳሮቶች መካከል መረጃ ለጋዜጠኞች ተደራሽ ከማድረግ አንፃር በመንግሥት በኩል ክፍተት መኖሩ እና የሚሰጠው መረጃ የአንድ ወገን መሆኑ በዋነኝነት መረጃን የማግኘት መብት ላይ ተጽዕኖ የፈጠረ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ በተለይ በዚህ ዲጂታል ዘመን የበይነመረብን በመጠቀም የዜጎች መረጃ ማሰራጨት “ጋዜጠኛ ማነው?” የሚለውን ጥያቄ ማስነሳቱ በብዙ አካላት ዘንድ መደናገር መፈጠሩ እንዲሁም የመረጃ ተአማኒነት እና የጋዜጠኝነት ሙያ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል የሚሉ ሃሳቦች ተንጸባርቀዋል፡፡ 

በሌላ በኩል የሳንሱር እና የጋዜጠኝነት ደህንነትን በተመለከተ ከተጠቀሱት አንኳር ሃሳቦች መካከል የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነት፣ በአጠቃላይ በጋዜጠኞች ላይ የተጋረጠው የደህንነት ስጋት፣ የሚዲያ ምህዳሩ እየሰፋ የመጣ ቢሆንም የጋዜጠኞችና የሚዲያ ተቋማት አቅም አነስተኛ መሆን፣ እንዲሁም እራስን ሳንሱር ማድረግ (Self-censorship) ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ፣ የፕሬስ ነፃነት እና የመረጃ ተደራሽነት መብቶች ላይ ተጽዕኖ መፍጠሩ ተጠቅሰዋል፡፡ 

በውይይቱ ከተነሱት ተግባራዊ ተሞክሮዎች ውስጥ የሴት ጋዜጠኞችን ከሚያጋጥማቸው ችግሮች መካከል ለሥራ እና እድገት ላይ የሚፈጸምባቸው መድሎ፣ ጠንካራ፣ ሞጋች፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ለወንድ ባለሙያዎች መስጠት፣ ከወሊድ እረፍት በኋላ ወደ ቀድሞ ስራ ለመመለስ መገለል እና ከሚዘግቧቸው ጉዳዮች ይልቅ ፆታን መሰረት ያደረገ ትችቶች በዋነኝነት ተነስቷል፡፡

በውይይቱ የተነሱ ምክረ-ሀሳቦች እና የወደፊት የመፍትሔ አቅጣጫዎች መካከል የፕሬስ ነፃነት እና ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ላይ የሚደረጉ ገደቦች ሕገ-መንግሥታዊ እና ዓለምአቀፍዊ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ መሆን እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡ በአጠቃላይ ሁሉን አቀፍ የሆነ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማሻሻል ተገቢ እንደሆነ ታምኖበታል፡፡ 

የውይይት መድረኩ ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የሲቪል፣ ፖለቲካ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጅብሪል አንደገለጹት አዎንታዊ ለውጦችም ተግዳሮቶችም አንዳሉ እውቅና መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ እና የፕሬስ ነጻነትን በተሻለ መልኩ ለመጠበቅ እንደ ማህበረሰብ በትብብር መስራት እንዳለብን አሳስበዋል፡፡

ሰመራ
ኢሰመኮ በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በአፋር እና በአማራ ክልል በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ባከናወነው ምርመራ ሪፖርት የለያቸው ግኝቶች እና ምክረ-ሃሳቦች ላይ ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ለመፍጠር እና በመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ውስጥ የሴቶችን ሁለንተናዊ ጥቅም እና ተሳትፎ ማረጋገጥን ዓላማው ያደረገ የውይይት መድረክ በሚያዝያ 27 እና 28 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰመራ ከተማ ተካሂዷል፡፡  

የውይይት መድረኩ በሚያዝያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም. በኢሰመኮ የሴቶች እና ሕፃናት መብቶች ኮሚሽነር መስከረም ገስጥ እና የሲቪል፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ መብቶች ኮሚሽነር አብዲ ጂብሪል የተመራው እና ከአፋር ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የተካሄደውን ውይይት ተከትሎ የተከናወነ ነው፡፡

በውይይቱ በአፋር ክልል ፍንቲ ረሱ፣ ኪልበርቲ ረሱ እና አውረሲ ረሱ ዞኖችና ወረዳዎች የሚገኙ የፍትሕ አካላት፣ የጤና ቢሮ፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ሴቶች እና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ፣ ሴቶች ማኅበራት የመጡ ተወካዮችን ጨምሮ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ልዩ ልዩ ሀገር በቀል እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡ ይህ ውይይት ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም በክልል ደረጃ በባህር ዳር ከተማ ፤ እንዲሁም በፌደራል ደረጃ  በአዲስ አበባ ከተማ ያከናወናቸው መድረኮች አካል ነው፡፡

በመድረኩ ኮሚሽኑ በሰሜን ኢትዮጵያ ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ በአፋር እና አማራ ክልሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በሚመለከት ባደረገው ምርምራ ሪፖርት የተለዩትን ግኝቶችና ምክረ ሃሳቦች መሠረት በማድረግ ግጭቱ በሴቶች ላይ ያስከተለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሚመለከቱ ግኝቶችና ምክረ ሃሳቦች ለባለ ድርሻ አካላቱ ተጠቃሎ ቀርቧል፡፡ 

በቀረበው የተጠቃለለ ሪፖርት ላይ ባለድርሻ አካላቱ በቀጣይ የሚጠበቅባቸውን ሚና በመለየት የኮሚሽኑን ምክረ-ሃሳቦች ተፈጻሚነት ለማገዝና ለመከታተል፤ በመልሶ ማቋቋም ሂደት ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጠናከር፣ እንዲሁም ለተጎጂ ሴቶች መብቶች መጠበቅና የድጋፍ ተደራሽነትን ለማስፈን የሚያስችሉ የተደራጀ ስልታዊና ቅንጅታዊ አሠራር ለመዘርጋት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ 

የኢሰመኮ የሰመራ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ኡስማን አህመድ “የመልሶ ማቋቋም ሥራዎችን ስልታዊ በሆነ መልኩ አቀናጅቶ ለማስኬድ ስምምነት ላይ መደረሱ በክልሉ ለተፈጠረው የሰብአዊ መብቶች ቀውስ የሚደረገውን ምላሽ ውጤታማ ያደርገዋል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ አክለውም  “የሚከናወኑ የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች በቀጥታ ከግጭቱ ማግስት በሚኖረው የሴቶች መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድር በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ማከናወን ያሻል” ብለዋል።  

በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢሰመኮ ሴቶች እና ሕፃናት መብቶች ኮሚሽነር መስከረም ገስጥ “በመልሶ ማቋቋም ሂደት ውስጥ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፤ ሂደቱም የተጎጂዎቹን ልዩ ፍላጎት ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ሊከናወን ይገባል” ብለዋል፤ በተጨማሪም “የመልሶ ማቋቋም ሥራዎችን በተቀናጀ መልክ አስተሳስሮ ማከናወን ያስፈልጋል” ሲሉ አሳስበዋል።

Related posts

February 3, 2022August 28, 2023 Press Release
በኢሰመኮ እና በUNOHCHR አዘጋጅነት በሁለቱ ተቋማት የትግራይ ክልል ግጭትን በተመለከተ የተደረገውን ጣምራ ምርመራ ሪፖርት ምክረ ሃሳቦች አፈጻጸምና ክትትል አስመልክቶ የተካሄደ የምክክር መድረክ
July 22, 2022October 6, 2022 Event Update
ኢሰመኮ በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት በአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ላይ የደረሰውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በተመለከተ በአማራ ክልልና በአፋር ክልል የተለያዩ ከተሞች ባደረገው ክትትል የተገኙ ግኝቶች እና ምክረ ሃሳቦች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄዱ የምክክር መድረኮች
December 10, 2021August 26, 2023 EHRC Quote
ኢሰመድህ ከተ.መድ. የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የምስራቅ አፍሪካ ጽ/ቤት (UNOHCHR - EARO) ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መርኃ ግብር ለኢሰመኮ ምስጋና አቀረበ
January 27, 2023January 27, 2023 Event Update
ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሔዎችን የማመቻቸት ሥራዎች የሰብአዊ መብቶች መርሆችን መሠረት ያደረጉ እንዲሆኑ ማስቻል

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.