Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ኤፕለፕሲ እና ሰብአዊ መብቶች

February 13, 2023August 28, 2023 Explainer

ኤፕለፕሲ ያለባቸው ሰዎችና ቤተሰቦቻቸው ለከፍተኛ መገለልና መድሎ የተጋለጡ መሆናቸውን ከግምት በማስገባት፤ ስለሕመሙ ያሉ የተሳሳቱ አመለካከቶች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠርና መብቶቻቸውን ለማስከበር ሲባል በዓለም አቀፍ ደረጃ የካቲት ወር ሁለተኛው ሰኞ ዓለም አቀፍ የኤፕለፕሲ ቀን ሆኖ ይታወሳል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

ማብራርያ

ኤፕለፕሲ እና ሰብአዊ መብቶች

በዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሠረት በዓለም ላይ ከ50 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ኤፕለፕሲ (በተለምዶ የሚጥል ሕመም ተብሎ የሚታወቀው) አለባቸው፡፡ ከዚህ ውስጥ ወደ 80% የሚጠጉት ዝቅተኛ ወይም መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡

ኤፕለፕሲ ያለባቸው ሰዎችና ቤተሰቦቻቸው ለከፍተኛ መገለልና መድሎ የተጋለጡ መሆናቸውን ከግምት በማስገባት፤ ስለሕመሙ ያሉ የተሳሳቱ አመለካከቶች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠርና መብቶቻቸውን ለማስከበር ሲባል በዓለም አቀፍ ደረጃ የካቲት ወር ሁለተኛው ሰኞ ዓለም አቀፍ የኤፕለፕሲ ቀን ሆኖ ይታወሳል፡፡ የዚህ ዓመት የኤፕለፕሲ ቀን ትኩረቱን ኤፕለፕሲ ያለባችው ሰዎች ላይ የሚደርሰው መገለል እና መድሎ ላይ በማድረግ ሰኞ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. በተለያዩ ፕሮግራሞች ታስቦ የሚውል ሲሆን በኢትዮጵያም ‹‹በጋራ በሚጥል ሕመም ላይ ያለውን መድሎ እና መገለል እናቁም›› በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡ ይህ የኢሰመኮ ማብራሪያ ይህንኑ ቀን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ኤፕለፕሲ ያለባቸው ሰዎች እና ሰብአዊ መብቶቻቸውን በተመለከተ ግንዛቤን ለመፍጠር ይረዳል:: 

ኤፕለፕሲ ምንድን ነው?

ኤፕለፕሲ ማለት የአእምሮ ተግባር እና ብቃትን በድንገት በማወክ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ራስን መሳት እና ከራስ ቁጥጥር ውጪ የሆነ የእጅና እግር መወራጨትን ወይም ራስን ሳይስቱ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የአካል እንቅስቃሴን የሚያስከትል ሕመም ነው፡፡ ኤፕለፕሲ በተለምዶ የሚጥል ሕመም ተብሎ የሚጠራ ቢሆንም ራስን በመሳት ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የሰውነት መወራጨት እና መውደቅን የማያስከትል የኤፕለፕሲ አይነትም አለ። ይህ የሚከሰተው በአእምሮ ውስጥ ያሉ የነርቭ ሕዋሳት ከተለመደው የነርቭ ሥርዐት ውጭ ኃይለኛ እና ፈጣን ኤሌክትሪክ ቻርጅ በሚያስተላልፉበት ወቅት ለተወሰነ ጊዜ የአእምሮን የተለመደ ተግባር በመረበሽ ወይም በማስተጓጎል የሰዎች ፀባይ እንዲለዋወጥ፣ በእንቅስቃሴ ላይ ችግር እንዲፈጠር፣ የስሜት መረበሽና አለመረጋጋት እንዲኖር፣ የአእምሮን የማሰብ ተግባር በማስተጓጎል መናድ (መውደቅና መንቀጥቀጥ) እንዲፈጠር የሚያደርግ ሕመም ነው፡፡ ኤፕለፕሲ በሁሉም የዕድሜ ደረጃ ሊከሰት የሚችል በአንጎል ላይ ከሚከሰቱ የተለመዱ የአካል ጉዳት ዓይነቶች አንዱ ነው፡፡

ምንም እንኳ የኤፕለፕሲ መንስዔዎችን በትክክል ማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም ኤፕለፕሲ የተለመዱ ተብለው ከተለዩ ምክንያቶች መካከል በጭንቅላት ላይ የሚደርስ አደጋ፣ የጭንቅላት ኢንፌክሽን፣ ከፍተኛ ትኩሳት፣ በፅንስ ላይ የሚያጋጥም የኦክሲጅን እጥረት፣ የአንጎል እጢ፣ ተፈጥሯዊ የአእምሮ ጉዳት፣ አልኮል መጠጦች እና አደንዛዥ ዕጾች ወይም ስትሮክ ሊሆን ይችላል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የኤፕለፕሲ ሁኔታ ምን ይመስላል?

ምንም እንኳን ኤፕለፕሲን በተመለከተ በቅርብ ጊዜ የተጠናቀረ ሀገራዊ መረጃ ባይኖርም በ1997 ዓ.ም. የተደረገ ጥናት የሚያሳየው ከ624,000 በላይ ሰዎች ኤፕለፕሲ ያለባቸው መሆኑን እና በአንድ ዓመት ውስጥ በኢትዮጵያ ከ76,800 በላይ አዳዲስ ታማሚዎች እንደሚገኙ ነው፡፡[1] ኤፕለፕሲ ታማሚውን ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ አባላት ላይም ተጽዕኖ ያሳድራል:: ስለሆነም በሀገራችን ከ2,184,000  በላይ የቤተሰብ አባላት ኤፕለፕሲ ያለበትን ሰው በመንከባከብ እና ተጓዳኝ ችግሮችን በመጋፈጥ ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል::[2]

በኢትዮጵያ ኤፕለፕሲ ካለባቸው ሰዎች መካከል ወደ ሕክምና ተቋማት የሚሄዱት 5% ብቻ ሲሆኑ፤ 95% የሚሆኑት የሕክምና አገልግሎት የማያገኙ ናቸው፡፡[3] ሁኔታውን አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ በሕክምና ተቋማት በቂ ሕክምና አለመኖሩ፣ በሕብረተሰቡ ውስጥ ስለሕመሙ ያለው የተሳሳተ አመለካከት እና በሕመሙ ላይ የሰለጠነ ባለሙያ እጥረት መኖሩ ነው፡፡ በተለይ ኤፕለፕሲ ያለባቸው ሕፃናት በቂ የትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ስለማይደረግና በቂ ድጋፍ ስለማይኖራቸው ለመሥራት የሚችሉበት ዕድሜ ላይ ሲደርሱ ዝቅተኛ የሥራ ዕድል እንዲኖራቸውና በድህነት እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡

ኤፕለፕሲ ያለባቸው ሰዎች ለብቻቸው ቤት ውስጥ በሚሆኑበት እና በተለይም የተለያዩ የቤት ውስጥ ሥራዎችን በሚሰሩበት አጋጣሚ በድንገት ለመውደቅ እና የእሳት ቃጠሎን፣ በስለታማ ነገሮች መጎዳትን ጨምሮ ለተለያዩ ተጨማሪ አካል ጉዳቶች ይጋለጣሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኤፕለፕሲ ያለባቸው ሰዎችን በተመለከተ በማኅበረሰባችን ውስጥ ያለው አሉታዊ አመለካከትና የተዛባ እሳቤ ሥር የሰደደ በመሆኑ ጉዳቱ ያለባቸው ሰዎች በልዩ ልዩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሙሉና አስተማማኝ ተሳትፎ እንዳያደርጉ ከፍተኛ ተግዳሮት ይሆንባቸዋል፡፡


በኤፕለፕሲ እና በሰብአዊ መብቶች መካከል ያለው ግንኙነት ምንድነው?

በዓለም አቀፉ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት መሠረት አካል ጉዳተኞች ስንል የተለያዩ መሰናክሎች ከሚያስከትሏቸው ተጽእኖዎች የተነሳ ከሌሎች ሰዎች ጋር በእኩልነት በማኅበረሰቡ ውስጥ ሙሉ እና ውጤታማ ተሳትፎ እንዳያደርጉ ሊገድቡ የሚችሉ የረዥም ጊዜ የአካል፣ የአእምሮ፣ የአእምሯዊ እድገት ውስንነት ወይም የስሜት ሕዋሳት ጉዳቶች ያሉባቸውን ያካትታል፡፡ የአፍሪካ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ፕሮቶኮል ደግሞ አካል ጉዳተኞች የሚባሉት ከአእምሮ ጤና እና እድገት ውስንነት በተጨማሪ የኒውሮሎጂ ጉዳት ያለባቸው እና ከሌሎች ጋር እኩል ተሳትፎ እንዳያደርጉ የሚገድቡ ተግዳሮቶች ያሉባቸው መሆናቸውን በግልጽ ዕውቅና ይሰጣል፡፡ 

በእነዚህ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ስምምነቶች መሠረት ኤፕለፕሲ የኒውሮሎጂ ጉዳት ከሚያስከትላቸውና በአብዛኛው ከማይታወቁ አካል ጉዳቶች መካከል አንደኛው ነው፡፡ ኤፕለፕሲ ያለባቸው ሰዎችም በማኅበረሰባቸው ውስጥ ከሌሎች ጋር በእኩልነት ሙሉና አስተማማኝ ተሳትፎ ለማድረግ እንቅፋት የፈጠሩ የአመለካከትና ከባቢያዊ መሰናክሎች የሚያጋጥሟቸው በመሆኑ፣ ሥር የሰደደ ማኅበራዊ መድሎና መገለል የሚደርስባቸው በመሆኑ እንዲሁም የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን ለማከናወን በርካታ ተግዳሮቶች የሚያጋጥሟቸው በመሆኑ በዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እና ሀገራዊ ሕጎች ዕውቅና የተሰጣቸው ሰብአዊ መብቶቻቸው በመጣስ ላይ ይገኛሉ፡፡

ኤፕለፕሲ ያለባቸው ሰዎች የተሟላ የሕክምና አገልግሎት የማግኘት፣የመማር እና የመሥራት መብት አላቸው፡፡ በሀገራችን ሥር ሰዶ በሚገኘው አሉታዊ አመለካከት የተነሳ እነዚህን የሕብረተሰብ ክፍሎች ለመንከባከብ ከጤና ተቋማት ይልቅ ባህላዊ መንገዶች የሚመረጡ በመሆኑ ፤ በጤና ተቋማትም ቢሆን የሚሰጠው የሕክምና አገልግሎት በቂ ባለመሆኑና በዚህ ሕመም ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶችም የእንክብካቤ ማእከላት በበቂ ሁኔታ የሌላቸው በመሆኑ ኤፕለፕሲ ያለባቸው ሰዎች በቂ ሕክምና አያገኙም፡፡ ስለሆነም በዚህ ሕመም ምክንያት መድሎ ሳይደረግባቸው መንግሥት ለሌሎች ሰዎች የሚያቀርበውን ዓይነት የጥራት ደረጃ ያለው ነጻ ወይም የመክፈል ዐቅምን ያገናዘበ የጤና እንክብካቤ መስጠት፣ በወቅቱ ሕሙማንን መለየትና ማከም፣ አካል ጉዳትን ለመቀነስና ተጨማሪ የአካል ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል የተዘጋጁ አገልግሎቶችን መስጠት፣ የጤና አገልግሎቶችን ገጠርን ጨምሮ በሁሉም ቦታ ተደራሽ ማድረግ እና ለጤና ባለሙያዎች የዐቅም ግንባታ ስልጠና የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡

ኤፕለፕሲ ያለባቸው ሰዎች ግለሰባዊ ነጻነትና በማኅበረሰቡ ውስጥ የመካተት እንዲሁም ንቁ ተሳትፎ የማድረግ መብት አላቸው፡፡ ሆኖም ግን በማኅበረሰቡ ውስጥ ሰፍኖ በሚገኘው የተሳሳተ አመለካከት ምክንያት ኤፕለፕሲ ያለባቸው ሰዎች ከፍተኛ የሆነ ማኅበራዊ መገለልና መድሎ ይደርስባቸዋል። ማኅበራዊ ተሳትፎም እንዳይኖራቸው እና በራሳቸው ጉዳይ ላይ ሐሳባቸውን እንዳይሰጡ ይደረጋል፡፡ በአብዛኛው በቤተሰቦቻቸው ላይ በጥገኝነት እንዲኖሩ ይገደዳሉ፡፡

አካታች የትምህርትና የሥራ ዕድል መብትን በተመለከተ ኤፕለፕሲ ያለባቸው ሰዎች በሕመሙ ምክንያት በትምህርትና በሥራ ገበታ ላይ የማይገኙበት ጊዜ በመኖሩ፣ ሕመሙ በድንገት ያጋጥመኛል በሚል ፍርሀት ትምህርታቸው ወይም ሥራቸው ላይ ትኩረት ማድረግ ስለሚሳናቸው እና በማኅበረሰቡ ውስጥ ባለው አሉታዊ አመለካከት የተነሳ ከትምህርት እና ከሥራ የተገለሉ በመሆናቸው ያለባቸውን የአካል ጉዳት ከግምት ያስገባ፣ ብዝሀነትን ሊያስተናግድ የሚችል፣ ተደራሽና ባህላቸውን ያከበረ አካታች ትምህርት እና የሥራ ሁኔታን መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

በአጠቃላይ ኤፕለፕሲ ያለባቸው ሰዎች ሰብአዊ መብቶቻቸውን ሙሉ ለሙሉ እንዲጠቀሙ ከመድሎና መገለል እንዲጠበቁ፣ እኩል የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ የጤና አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ አካታች ትምህርት የማግኘት መብታቸው እንዲከበር የአመለካከት፣ ከባቢያዊና ተቋማዊ ዕንቅፋቶችን ማስወገድ እና ተመጣጣኝ ማመቻቸቶችን ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡


[1] Tekle-Haimanot R, Forsgren L, Ekstedt J. Incidence of epilepsy in rural central Ethiopia. Epilepsia. 1997 May;38(5):541-6. doi: 10.1111/j.1528-1157.1997.tb01138.x. PMID: 9184599.)

[2] Ethiopia Socioeconomic Survey 2018–2019 accessed on https://www.fao.org/3/cc0137en/cc0137en.pdf

[3] Visit CareEpilepsy website http://care-epilepsy.org/epilepsy-facts-ethiopia/ (accessed on Feb.08/2023)

Related posts

April 24, 2023September 30, 2023 Explainer
በሽግግር ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ የአረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ተሳትፎ እና ተካታችነት
June 8, 2023August 28, 2023 Event Update
በሕግና ፖሊሲ ቀረጻ እንዲሁም ትግበራ ሂደቶች ውጤታማ የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ እንዲኖር ስለማስቻል
November 6, 2023November 16, 2023 Expert View
ዲስሌክሲያ ላለባቸው ሰዎች ልዩ ፍላጎት ያማከለ የትምህርት ሥርዓት፣ የሕክምና ማእከሎች እና የምርመራ መመዘኛዎች ሊኖሩ ይገባል
February 9, 2022August 28, 2023 Human Rights Concept
የሴት ልጅ ግርዛትና ሰብአዊ መብቶች

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.