Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ኮሚሽኑ የሚያቀርባቸው ምክረ ሐሳቦች በመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ተግባራዊነታቸው እንዲረጋገጥ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል

May 8, 2023June 11, 2024 Press Release

በአማራ ክልል ያለው ወታደራዊ እርምጃና የሰብአዊ መብቶች እንደምታው፣ የዘፈቀደ እስርና ተገቢ ያልሆነ አያያዝ፣ ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል አጠቃቀም፣ በሚዲያና ተቃዋሚዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት፣ ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀሰ መብት ላይ የተጣለ የዘፈቀደ ገደብ፣ ሕጋዊ ሂደትን ያልተከተለ የቤቶች ፈረሳ፣ በግዳጅ ማስነሳትና የኑሮ ውድነት የተነሳ የደረሰው እንግልትና የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲሁም በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ማቋቋም አሳሳቢነታቸው ከቀጠሉ ጉዳዮች ውስጥ ይገኛሉ

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የ2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት የ9 ወር የሥራ ክንውን ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. አቅርቧል፡፡ ኮሚሽኑ ባቀረበው የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባደራጃቸው ዘጠኝ የትኩረት መስኮች የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተገኙ ውጤቶች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በዝርዝር ተካትተዋል፡፡

በቀረበው ሪፖርት የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራን በተመለከተ ኮሚሽኑ በዋናው መሥሪያ ቤቱና በከተማ ጽሕፈት ቤቶቹ በ1491 ሰዎች 1680 ጉዳዮች ላይ አቤቱታ የቀረቡለት ሲሆን ከነዚህም መካከል በኮሚሽኑ ሥልጣን ሥር የሚወድቁ 1084 አቤቱታዎችን ተቀብሎ ማስተናገዱ ተገልጿል፡፡ አቤቱታ ከቀረበባቸው ጉዳዮች መካከል አብዛኞቹ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶችን የተቀሩት ደግሞ የኢኮኖሚያዊና የማኅበራዊ መብቶችን የተመለከቱ ናቸው።

ኮሚሽኑ በ48 ማረሚያ ቤቶች እና በ323 ፖሊስ ጣቢያዎች ባካሄደው የክትትል ሥራ ለይቶ ባስቀመጣቸው ግኝቶች እና በሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች መሠረት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እና ያለበቂ ማስረጃ በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎች መፈታታቸውን፣ የዋስትና መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው መደረጉን፣ ኢ-ሰብአዊ አያያዝ ሲፈጽሙ የነበሩ የተወሰኑ የጸጥታ አባላት ተጠያቂ መደረጋቸውን፣ በመደበኛ ማረሚያ ቤቶች በእስር ላይ ያሉ ሰዎች መብቶች ጥበቃ እና አያያዝ መሻሻል ማሳየታቸው እና ለአብዛኛዎቹ አቤቱታዎች አወንታዊ መፍትሔ እንዲያገኙ መደረጉን ኮሚሽኑ ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት ጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል በሪፖርት ዘመኑ ኮሚሽኑ በደረሱት አቤቱታዎችና በራሱ አነሳሽነት በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል፣ በአፋር፣ በሱማሌ፣ በአማራ እና ደቡብ ክልሎች በሚገኙ 59 የተፈናቃይ እና የስደተኞች መጠለያዎች፣ እንዲሁም ከማኅበረሰቡ ጋር የሚኖሩ ተፈናቃዮች እና የተመላሾች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ክትትል አድርጓል፡፡

ከምርመራ ሥራ ጋር በተገናኘ ኮሚሽኑ በጋምቤላ ከተማ በነበረው ውጊያ የተነሳ በደረሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምርመራ ሪፖርት ይፋ ማውጣቱን፤ የሴቶች (ከኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች አንጻር) እና ሕፃናት መብቶች የሚመለከቱ የሕግ ማዕቀፎች እና በአተገባበር ረገድ ያሉ ክፍተቶችን ለመለየት የሚያስችሉ ምርምር/ጥናት መደረጉን፣ በሴቶችና ሕፃናት መብቶች ዙሪያ ፖሊሲ/ሕጎች ላይ የምክር አገልግልት መሰጠቱን እና ያልጸደቁ ስምምነቶች እንዲጸድቁ የውትወታ ሥራ መከናወኑን ለምክር ቤቱ በቀረበው የሪፖርት ማብራሪያ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም በሕገወጥ እና በዘፈቀደ እስር ላይ ትኩረቱን ያደረገ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው በሕዝብ ፊት የሚካሄድ ብሔራዊ/ግልጽ የምርመራ መድረክ በሃዋሳ፣ በጂግጅጋ፣ በባሕር ዳር እና በአዳማ ከተማ ተዘጋጅቷል፡፡ በደቡብ ክልል በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ወቅት እና በድኀረ ምርጫ በወረዳዎች እና ዞኖች የሰብአዊ መብት አያያዝን በተመለከተ ክትትል በማድረግ ሁለት ሪፖርቶች ተዘጋጅተዋል።

በማኅበራዊ እና በኢኖሚያዊ ዘርፍ የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኞች መብቶች አተገባበር ዙሪያ የክትትል ሪፖርት ማውጣቱን እና በሪፖርቱ የተዘረዘሩ ምክረ ሐሳቦች በአዲስ አበባ፣ በባሕር ዳር፣ በሃዋሳ እና በጅማ ከተሞች ተግባራዊ መደረጋቸውን ለመገምገም በተደረገ የምክክር መድረክ ሪፖርቱ ከወጣ በኋላ የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሠራተኞች መብቶች አጠባበቅ መሻሻላቸውን ለመረዳት መቻሉን ኮሚሽኑ በሪፖርቱ ገልጿል፡፡

ኮሚሽኑ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የምሥራቅ አፍሪካ ጽ/ቤት (UNOHCHR – EARO) ጋር በመተባበር በተለያዩ ግጭቶች ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ከሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ በሰላም እና ጸጥታ ላይ ከሚሠሩ የሲቪል ማኅበራት፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች ጋር የሽግግር ፍትሕን የተመለከተ 15 የመስክ ምክክሮችን አድርጓል። የማኅበረሰብ ምክክሮችን መሠረት በማድረግ፣ የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማዕቀፍን ለማዳበር ይረዳሉ የተባሉት ዋና ዋና ግኝቶች፣ ምክረ ሐሳቦች እና የፖሊሲ ማዕቀፍን በመንደፍም ሆነም በመተግበር ሂደት ውስጥ በአትኩሮት ሊጤኑ የሚገባቸው ዓለም አቀፍ መርሆችን ያካተተ መሪ ሰነድ (Advisory document) ተዘጋጅቶ ይፋ መደረጉ ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም በሽግግር ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ የአረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ተሳትፎ እና ተካታችነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ለመውሰድ የውትወታ ሥራዎች ተከናውነዋል። ኮሚሽኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ያከናወነውን የአረጋውያን እንክብካቤ ማእከላት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሪፖርት ይፋ ያደረገውም በዚሁ የሪፖርት ወቅት መሆኑ ተገልጿል።

በተመሳሳይ በሴቶችና ሕፃናት መብቶች ዙርያ የተሠሩ ክትትሎች እና ይፋ ከተደረጉ ሪፖርቶች በተጨማሪ በተለይም በቂ የኑሮ ደረጃ በማግኘት፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን የተመለከቱ ክትትሎች መታቀዳቸውን በሪፖርቱ ተመላክቷል። በሁሉም ክልሎች የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ክትትሎች በሪፖርቱ ወቅት መሠራታቸውን የገለጸው ኢሰመኮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተለዩ ግኝቶች ላይ ተመሥርቶ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር የውትወታ ሥራ በመሥራት ላይ ማተኮሩ ተገልጿል። በአጋርነት፣ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን እና በተቋም ግንባታ የተሠሩ ሥራዎችም ተጠቅሰዋል። በሰብአዊ መብቶች ትምህርት ዘርፍም በዘጠኝ ወራት በስድስት ክልሎች የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት፣ በሀገር ውስጥ ተፈናቃይ፣ በአካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች እንዲሁም በሴቶች እና ሕፃናት መብቶች ላይ ለሚሠሩ ሲቪል ማኅበራት አባላት በአጠቃላይ 2000 ለሚጠጉ ሰዎች የአሰልጣኞች ስልጠናን ጨምሮ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫና ስልጠናዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ በሌላ በኩል በኢንተርኔት አማካኝነት በሚተላለፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርታዊ መልዕክቶች በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ተደራሽ መሆን መቻሉ ተመላክቷል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ባለፉት ዘጠኝ ወራት “በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ግጭት በሰላም ለመቋጨት የተደርገው ስምምነት፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ እና በቤንሻንጉል ክልሎች ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው ጥረት፣ የሽግግር ፍትሕን ተግባራዊ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎችና ምክክሮች፣ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የተወሰዱ የተወሰኑ እርምጃዎች ለምሳሌ በጋምቤላ ክልል፣ እንዲሁም በሃዋሳ፣ በጅግጅጋ፣ በባሕር ዳር እና በአዳማ ከተሞች በመንግሥት ተሳትፎና በሕዝብ ፊት በግልጽ የተካሄዱ ብሔራዊ የምርመራ ሂደቶች፣ የሰብአዊ መብቶች ትምህርትን በመደበኛ ትምህርት ሥርዓት ለማካተት ኮሚሽኑ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የጀመራቸው ሥራዎች፣ የደቡብ ክልል ምርጫ ከመጠነኛ ሥነ-ሥርዓታዊ ግድፈቶች ውጪ የሰብአዊ መብቶች በተከበሩበት ሁኔታ መካሄዱ ጥሩ ተስፋ ሰጪ እርምጃዎችና ጅማሮዎች መሆናቸውን” ገልጸዋል፡፡

ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም “በአንጻሩ በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴና የሰብአዊ መብቶች እንደምታው፣ የዘፈቀደ እስርና በእስር ወቅት የሚደርስ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ፣ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች የሚወስዱት ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ፣ በጋዜጠኞች፣ በሚዲያ፣ በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ተቃዋሚ ድምጾች ላይ ያነጣጠረ ጥቃትና የቅድመ ክስ እስር፣ ከቦታ ወደ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት ላይ የተጣሉ የዘፈቀደ ገደቦች፣ በድርቅ፣ ሕጋዊ ሂደትን ያልተከተለ የቤቶች ፈረሳ እና በግዳጅ ማስነሳት አሳሳቢ ጉዳዮች ሆነው ቀጥለዋል” ሲሉ አብራርተዋል። በተመሳሳይ “በከፍተኛ የኑሮ ውድነት የተነሳ በሕዝብ ላይ የደረሰ እንግልትና የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ጥሰቶች፣ በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን እና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን (በተለይም የትምህርትና የጤና አገልግሎት) መልሶ ለማቋቋም ገና ብዙ ሥራ የሚጠብቅ መሆኑ እና እነዚህ ሁሉ ችግሮች በሴቶች፣ በሕፃናት፣ በአካል ጉዳተኞችና በአረጋውያን ላይ ተደራራቢ ለሆኑ የመብት ጥሰቶች የሚያጋልጥ መሆኑን” ዋና ኮሚሽነሩ አስረድተዋል። በተጨማሪም “ኮሚሽኑ የፖሊስ ጣቢያዎችንና ሌሎች መደበኛ ያልሆኑ ሰዎች የታሰሩባቸውን ቦታዎች በቀላሉ ለመጎብኝት አለመቻሉና የበጀት አቅም ውስንነት አሳሳቢ ሆነው እንደቀጠሉ” ገልጸዋል።

በመጨረሻም ዶ/ር ዳንኤል ምክር ቤቱ የኮሚሽኑን ምክረ ሐሳቦች በየደረጃው ባሉ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ተፈጻሚነታቸውን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሊሠራ ይገባል ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የተከበሩ የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በበኩላቸው ኢሰመኮ በማድረግ ላይ ላለው ጥረት ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበው በሪፖርቱ ላይ በርካታ ዝርዝር አስተያየቶችን ሰጥተዋል። በዚህም መሠረት የቋሚ ኮሚቴው አባላት ከሰጧቸው ምክረ ሐሳቦች መካከል በአንዳንድ አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ በምክር ቤቱ ልዩ ሪፖርት እንዲቀርብ እና ኮሚሽኑ የምክረ ሐሳብ አፈጻጸም በሚሠራበት ወቅት የቋሚ ኮሚቴው ተጨማሪ ድጋፍ እንዲደረግለት የሚሉት ይገኙበታል፡፡

Related posts

February 21, 2023February 21, 2023 Press Release
ኢሰመኮ ለመጀመሪያ ጊዜ ያከናወነውን የአረጋውያን እንክብካቤ ማእከላት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ሪፖርት ይፋ አደረገ
October 27, 2023October 31, 2023 Press Release
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. የኮሚሽኑን 2ኛ ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶችን ሁኔታ በተመለከተ ያወጣውን መግለጫ በተመለከተ
April 24, 2024April 24, 2024 Event Update
ጋምቤላ:- ከግንቦት 2015 ዓ.ም. አንስቶ በተከሰቱ ግጭቶች ላይ በተከናወነ ምርመራ ግኝቶችና ምክረ ሐሳቦች ላይ ውይይት ተካሄደ
January 25, 2021February 11, 2023 Press Release
ጋምቤላ ክልል፡ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ አፋጣኝ ትኩረት ይሻል

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.