የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 20(2) እና (4)
- የተከሰሱ ሰዎች የቀረበባቸው ክስ በቂ በሆነ ዝርዝር እንዲነገራቸው እና ክሱን በጽሑፍ የማግኘት መብት አላቸው።
- የቀረበባቸውን ማናቸውም ማስረጃ የመመልከት፣ የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅ፣ ለመከላከል የሚያስችላቸውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ እንዲሁም ምስክሮቻቸው ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲሰሙላቸው የመጠየቅ መብት አላቸው።
የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 14 (3) (መ)
- ማንኛውም ሰው በቀረበበት የወንጀል ክስ በተገኘበት የመዳኘት፣ ራሱን በግሉ ወይም በመረጠው ጠበቃ በኩል የመከላከል፣ ጠበቃ ከሌለው የሕግ አማካሪ እገዛ የማግኘት መብት ያለው መሆኑ እንዲገለጽለት እንዲሁም ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እና የገንዘብ ዐቅሙ የማይፈቅድ ሲሆን ያለክፍያ ጠበቃ እንዲመደብለት መብት አለው።