የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 14
- ማንኛውም ሰው ሰብአዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነትና የነጻነት መብት አለው።
የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 6(1) እና 7
- ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር ተፈጥሯዊ መብት አለው፡፡ ይህ መብት በሕግ ሊከበር ይገባል፡፡ ማንኛውም ሰው ያለአግባብ ሕይወቱን አያጣም፡፡
- ማንኛውም ሰው ለስቃይ ወይም ጭካኔ ለተሞላበት፣ ኢ-ሰብአዊ ወይም ክብርን ለሚያዋርድ አያያዝና ቅጣት ሊዳረግ አይገባም፡፡