ዓለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 19 (2)

  • ማንኛውም ሰው ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው። ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንም ዐይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል።

የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ አጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 34፣ አንቀጽ 19

  • መረጃ የማግኘት መብትን ተግባራዊ ለማድረግ ያመች ዘንድ የቃልኪዳኑ አባል ሀገራት ዜጎች ሊያውቋቸው የሚገቡ መንግሥታዊ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ይኖርባቸዋል። የዚህ መረጃ ተደራሽነት ለዜጎች ቀላል፣ ፈጣን፣ ውጤታማ እና ተግባራዊ እንዲሆን አባል ሀገራት ማንኛውንም ጥረት እንዲያደርጉ ይጠበቃል።