Areas of Work


የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ስደተኞች እና ፍልሰቶች መብቶች

ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከፍተና ቁጥር ያላቸውን ስደተኞች ከሚቀበሉ ሀገራት እንዷ፤ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙባት፤ እንዲሁም የበርካታ ስደተኞች መነሻ፣ ማለፊያ እና የፍልሰተኞች መዳረሻ በመሆኗ፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን፣ የስደተኞችን እና የፍልሰተኞችን መብቶች ማስፋፋት፣ መከበር እና መጠበቅን ማረጋገጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው።

ዋና ዋና የስትራቴጂክ ትግበራ ዘርፎች ምርምር እና ውትወታ፤ ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎች መብቶቻቸውን እንዲተይቁ ማብቃት፤ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ መስፈርቶች መከበራቸውን መከታተል፤ እንዲሁም የነዚህን የማኅበረሰብ ክፍሎች መብቶች እና ፍላጎቶች ለማስፋፋት ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረግ አጋርነትን ያካትታሉ።