- Version
- Download 4
- File Size 899.46 KB
- File Count 1
- Create Date November 9, 2026
- Last Updated November 9, 2026
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ የተከናወነ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሪፖርት
ኢሰመኮ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን (የምክክር ኮሚሽኑ) ባዘጋጃቸው ከግንቦት 2016 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 2018 ዓ.ም. በተካሄዱ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቶች እንዲሁም ከሐምሌ 8 እስከ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በተካሄደው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ክትትል አድርጓል። ክትትሉ ከአካታችነት፣ ከግልጽነት፣ ከተደራሽነት፣ ከአሳታፊነት፣ ከእኩልነት፣ ከገለልተኝነት፣ ሐሳብ ከመግለጽ ነፃነት፣ ከቅሬታ አፈታት ሥርዓት ተደራሽነት እና ውጤታማነት እንዲሁም ከሌሎች ተዛማጅ የሰብአዊ መብቶች መርሆዎች አንጻር ያለውን መጣጣም በመገምገም የተካሄደ ነበር።
ኢሰመኮ በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የአጀንዳ ማሰባሰብ ደረጃ ላይ በተከናወኑ ክትትሎች የተገኙ ዋና ዋና ግኝቶችንና ምክረ ሐሳቦችን በሁለት ዙር እንዲሁም በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የመጀመሪያዎቹ 15 ቀናት ክትትል የተገኙ ግኝቶችን ያካተተ ሦስተኛ ሪፖርት ለምክክር ኮሚሽኑ አቅርቧል።