Areas of Work


የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች

የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ፕሮግራም የመደራጀት እና የእንቅስቃሴ ነጻነትን፣ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ እና መረጃ የማኘት መብትን፣ በሕይወት የመኖር፣ የነጻነት እና የደኅንነት መብትን፣ በሕግ ፊት እኩል የመታየት እና በፖለቲካ ውስጥ የመሳተፍ መብትን፣ እንዲሁም ከአድልዎ እና ከማሰቃየት ተግባር የመጠበቅ መብትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች እንዲስፋፉ፣ መከበራቸውን እና መጠበቃቸውን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።

የሕግ የበላይነትን እና የዲሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ መሠራትዊ ማዕዘን የሆኑትን የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶችን ማስከበር እናዲሁም ለሚፈጸሙ ጥሰቶች ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ የምርመራ፣ የምርምር እና የውትወታ ሥራዎችን ጨምሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር በሚፈጠር አጋርነት እናጎለብታለን።