ማንኛውም የአስገድዶ መሰወር ተግባር ሰብአዊ ክብርን የሚጥስ ድርጊት ነው
ማንኛዋም ሴት ለሕይወቷ እና ለአካል ደኅንነቷ ክብር የማግኘት መብት አላት
ሁሉም ሰው ለግሉ እና ለቤት ውስጥ አገልግሎት በቂ የሆነ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ተቀባይነት ያለው፣ በአካል ተደራሽ እና በዋጋ ተመጣጣኝ የሆነ ውሃ የማግኘት መብት አለው
አባል ሀገራት ለአካል ጉዳተኞች ትምህርት የማግኘት መብት ዕውቅና ይሰጣሉ
እያንዳንዱ አባል ሀገር በሕግ ሥርዓቱ ውስጥ የማሰቃየት ተግባር ሰለባ የሆነ ሰው መፍትሔ እንደሚያገኝ እንዲሁም በተቻለ መጠን የተሟላ ማገገሚያን ጨምሮ ተፈጻሚነት ያለው ፍትሐዊና በቂ ካሳ የማግኘት መብት እንዳለው ማረጋገጥ አለበት