የሰብአዊ መብቶች ትምህርት እራሱ ሰብአዊ መብት እንደመሆኑ ሰብአዊ መብቶችን መሰረት ያደረገ ትምህርት በሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ እንዲካተት የማድረግ ጥረት የአትዮጵያ መንግሥት በዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ሀገር አቀፍ ደረጃ ከገባው ግዴታ ጋር የሚያያዝ ነው
የፕሬስና የሌሎች መገናኛ ብዙኃን፣ እንዲሁም የሥነ ጥበብ ፈጠራ ነፃነት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት አንቀጽ 29 ላይ ጥበቃ አግኝቷል
Freedom of the press and other mass media, and freedom of artistic creativity is guaranteed under article 29 of the FDRE Constitution
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መረጃ መሠረት እስከ ግንቦት 21 ቀን 2014 ድረስ 19 ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል
የምክረ ሃሳቦች አፈጻጸምን የመከታተልና ሪፖርት የማቅረብ ተቀዳሚ ኃላፊነት የመንግሥት ቢሆንም ሲቪል ማኅበራት ይህንን አስመልክቶ የራሳቸውን ምልከታ ሪፖርት ለማቅረብ ልዩ ዕድል አላቸው
በሚድያ አዋጁ አንቀጽ 86(1) የተመለከተው የቅድመ እስር ክልከላ ከአዋጁ አንቀጽ 3(1) እና 6(3) ጋርም ተቀናጅቶ ሲነበብ ለተመዘገበ ሚዲያ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ዓይነት ሚዲያዎች የተቀመጠ የሕግ ጥበቃ መሆኑን የሚያመለክት ነው
Female migrants told of a vicious circle of irregular migration where their human rights are put at risk as they continue to fall prey to smugglers and corrupted authorities
እነዚህ ታሳሪዎች እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ናቸው የተባሉ ሲሆን አራቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሕጻናት መደበኛ ላልሆነ የፍልሰት አዙሪት የተጋለጡ ሲሆን ይህም የሰብአዊ መብቶቻቸው አደጋ ላይ እንዲወድቅ፣ በሕገወጥ ደላሎች እና በሙስና ለተዘፈቁ ባለሥልጣናት ተጋላጭ ሆነዋል
የአካል ጉዳተኞች የሥራ ሥምሪት መብትን የሚመለከት አዋጅ የወጣ እና ሥራ ላይ የዋለ ቢሆንም፤ በተለያዩ የመንግሥት እና የግል ተቋማት ያለው ያልተጣጣመ አሠራር አካል ጉዳተኞች በሥራ ቅጥር፣ ዕድገት፣ ድልድል፣ ዝውውር፣ ሥልጠናና ሌሎች የሥራ ሁኔታዎች ወቅት መድልዎ እንዲደርስባቸው መንስኤ ነው
በወንጀል ክስ ምክንያት የታሰረ ወይም በቁጥጥር ስር የሚገኝ ማንኛውም ሰው በዳኛ ወይም በሕግ የዳኝነት ሥልጣን በተሰጠው አካል ፊት በአፋጣኝ የመቅረብ፤ እንዲሁም ተገቢ በሆነ ጊዜ ውስጥ ዳኝነት የማግኘት ወይም የመለቀቅ መብት አለው