የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ፣ በጾታ ዕኩልነት ላይ በአማካሪነት የሚሠሩት ወይዘሮ አሻም አሳዝነው፤ የጾታ ዕኩልነት አዶቮኬት የሆኑት ርብቃ ዳዊት እና ረዳት ፕሮፌሰር ሱራፌል ወንድሙ በውይይቱ ተሳትፈዋል
በተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ረገድ ያሉ ክፍተቶችን ለማረም ተጠያቂነትን የማረጋገጥ እና አሠራሮችን የማሻሻል ተግባራትን ማጠናከር ያስፈልጋል
የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ እና ሀገራዊ የምክክር መድረኩ ለማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች በቂ ትኩረት በሚሰጥ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ሊያደርጉ ይገባል
ኢሰመኮ የሰዎች እገታ እየተበራከት ነው አለ
ኢሰመኮ በዚህ መግለጫው የእገታ ጉዳዮች ለማሳያነት አቅርቧል
ታጣቂዎች የሚፈጽሟቸው የእገታ ተግባራት ከአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጋር የሚቃረን በመሆኑ ከድርጊታቸው መቆጠብ እንደሚኖርባቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኢሰመኮ አስታውቋል
የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የትምህርት መብት ለማረጋገጥ የመምህራንን ግንዛቤ በማዳበር የትምህርት አሰጣጡ ሰብአዊ መብቶችን መሠረት ያደረገ እንዲሆን ማስቻል ይገባል
የኢሰመኮ ተጠባባቂ ኮምሽነር ራኬብ መሰለ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች አሳሳቢ ሆኖ ለቀጠለው የእገታ ተግባር ዘላቂ በሆነ መልኩ እልባት ለመስጠት ለሰዎች እገታ መነሻና አባባሽ ምክንያት የሆነውን የሰላም መደፍረስና የትጥቅ ግጭትን በዘላቂነት በሰላማዊ መንገድ መፍታትን ጨምሮ ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባል” ብለዋል
በኢትዮጵያ በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የሚደርስ መፈናቀል እየተስፋፋ በመምጣቱ ይህን መሰል ሥጋት ያለባቸውን አካባቢዎች በመለየት እና በጉዳቱ ልክ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል
Improved coordination among stakeholders and active engagement of refugee-led organizations (RLOs) are important for safeguarding and realizing the rights of urban refugees