ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች ከሕግ ውጪ ታስረው የነበሩ 1,336 ሰዎች እንዲፈቱ ማድረጉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
ማንኛውም ሰው በሕገ መንግሥት ወይም በሌላ ሕግ የተሰጡትን መሠረታዊ መብቶች በመጣስ ለሚፈጸሙበት ድርጊቶች ሥልጣን ባላቸው የሀገር ውስጥ ፍርድ ቤቶች አማካኝነት ውጤታማ መፍትሔ የማግኘት መብት አለው
Everyone has the right to an effective remedy by the competent national tribunals for acts violating the fundamental rights granted him by the constitution or by law
ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2019 ዓ.ም. የምታዘጋጀው የአፍሪካ ብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋማት ትስስር (NANHRI) ጠቅላላ ጉባኤ እና በየሁለት ዓመቱ የሚያካሂደውን 16ኛው ኮንፈረንስ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ባለድርሻዎች ቀና ትብብር እና እገዛ እንዲያደርጉ፣ ኢሰመኮ የሚሰጣቸው ምክረ ሐሳቦች በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበሩ ኢሰመኮ ጥሪ ያቀርባል
EHRC calls upon stakeholders to extend full cooperation and support to ensure the successful hosting of NANHRI’s 2027 General Assembly and 16th Biennial Conference in Ethiopia, and urges the full implementation of its recommendations
በወንጀል ነክ ነገር ውስጥ ገብተው የተገኙ ሕፃናት ማቆያ እና ተሐድሶ ማእከላት ባለሙያዎች የሕፃናቱን ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ለማሻሻል እና ለሕፃናቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ጉልህ ሚና አላቸው
Personnel in rehabilitation and remand homes for children in conflict with the law play a vital role in strengthening children’s human rights protection and holistic development
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ እና የጋና የሰብአዊ መብቶችና የአስተዳደር ፍትሕ ኮሚሽን (CHRAJ) ከፍተኛ አመራሮች ተቋማዊ ትብብርን ለማጠናከር እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ የሚያስችል ውይይት አካሂደዋል
EHRC Chief Commissioner Berhanu Adello and CHRAJ senior officials engaged in a structured peer dialogue to discuss best practices and strengthen institutional cooperation
ኢሰመኮ ከአፍሪካ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ትስስር እና ከአባል ተቋማቱ ጋር በመተባበር 16ኛውን ዓመታዊ እና ጠቅላላ ጉባኤ በስኬት ለማስተናገድ ዝግጁ እና ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል