ኢትዮጵያን ጨምሮ በአለማችን ግጭቶች በሚደረጉባቸው አከባቢዎች ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመቃወም በሚል የተጀመረው የፊልም ፌስቲባል ዘንድሮም ለሶስተኛ ጊዜ መደረጉን ጀምሯል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የፊልም ዐውደ ትርኢት /ፌስቲቫል/፣ ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ፣ በዚኽ ሳምንት ተጀምሯል
ታኅሣሥ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው ዝግጅት የአጫጭር ፊልሞች እና የፎቶግራፍ ውድድር አሸናፊዎች ይፋ ተደርገዋል፣ ከታኅሣሥ 3 እስከ ታኅሣሥ 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ባሉት ቀናት በአሶሳ፣ በጋምቤላ፣ በሃዋሳ፣ በጅማ፣ በጅግጅጋ፣ በመቀሌ እና በሰመራ ከተሞች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይካሄዳል
በየዓመቱ ታኅሣሥ 10 የሚውለውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀን ለማሰብ የተጀመረው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የዘንድሮው በሕይወት የመኖር መብት እና በቂ የሆነ መኖሪያ ቤት በማግኘት መብት ላይ ያተኮረ ነው
All entries in all categories will receive due recognition, and winners will be announced during the opening ceremony of the 3rd edition of the Annual Human Rights Film Festival
ወጣቶች፣ ታዳጊዎች እንዲሁም የኪነጥበብ ዘርፍ ባለሞያዎች በውድድሩ እንዲሳተፉ ኮሚሽኑ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል
The 2023 edition of the Commission’s Human Rights Film Festival focuses on the rights to life and adequate housing. This year's celebration of International Human Rights Day on December 10 is particularly significant, as it marks the 75th anniversary of the Universal Declaration of Human Rights
የ2016 ዓ.ም. የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በሕይወት የመኖር መብት እና በቂ የሆነ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ ኅዳር 30 ቀን የሚውለው የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀን ዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብቶች መግለጫ 75ኛ ዓመት የሚታሰብበት ዝግጅት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፤ ሁሉም ሰው በውድድሩ እንዲሳተፍ እና ሂደቱን እንዲከታተል ተጋብዟል